በአርሶ አደር የምዝገባና ልየታ መመርያ ቁጥር 0...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በአርሶ አደር የምዝገባና ልየታ መመርያ ቁጥር 001/2013 ላይ ለወረዳ ዘርፍ አመራሮች፣ ለወረዳ ባለሙያዎችና ከየወረዳው ለተመረጡ የምዝገባና ልየታ ኮሚቴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

በአርሶ አደር የምዝገባና ልየታ መመርያ ቁጥር 001/2013 ላይ ለወረዳ ዘርፍ አመራሮች፣ ለወረዳ ባለሙያዎችና ከየወረዳው ለተመረጡ የምዝገባና ልየታ ኮሚቴዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

በስልጠናውም ላይ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አ/አ/ከ/ግ/ል/ፅ/ቤት ሀላፊ ተወካይ አቶ እዮብ እሸቱ፡የአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የአርሶ አደር መልሶ ማቅዋቃምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሳ ባይሳ ፡የወረዳ ዘርፍ አመራሮች፡ባለሙያዎች:የአርሶ አደር ምዝገባና ልየታ ኮሚቴዎች በመድረኩ ላይ ተሳታፊ እንደነበሩ ተገልጿል።

የአርሶ አደር መልሶ ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሳ ባይሳ የልማት ተነሽ አርሶ አደሮችን በመመርያ ቁጥር 001/2013 የምዝገባ መስፈርት መሰረት በመመዝገብ የአርሶ አደሩን ፍትሀዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።

ሌላው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ አ/አ/ከ/ግ/ል/ጽ/ቤ/ት ኃላፊ ተወካይ አቶ እዮብ እሸቱ ኮሚሽኑ የሠጠንን እድል በመጠቀም የልማት ተነሽ አርሶ አደሮች ምዝገባ በማከናወን  የአርሶ አደሩን የመልካም አስተዳደር ችግር እንደሚፈታ በመጥቀስ ለተግባሩ መሳካት ሁሉም አካል በተደራጀ አግባብ ሚናውን እንዲወጣና ተግባሩም በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments