
ሪፖርት ከዕቅድ ብቻ ሳይሆን ከቀደመ ሪፖርት ጋር ተናባቢ መሆን አለበት፡፡
ሪፖርት ከዕቅድ ብቻ ሳይሆን ከቀደመ ሪፖርት ጋር ተናባቢ መሆን አለበት፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን በጀነራል ካውንስል ግምገማ አድርጓል፡፡
ኮሚሽኑ በ2017 በጀት ዓመት አቅዶት የነበረውን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የአፈፃፀም ሪፖርቱን በየዘርፉ እንዲቀርብ አድርጎ ግምገማ አካሂዷል፡፡
በበጀት ዓመቱ የነበረውን ሂደትና ውጤት ከበጀት አፈፃፀም ጋር በማነፃፀር ግምገማ ያካሄደ ሲሆን ሪፖርት ከዕቅድ ብቻ ሳይሆን ከቀደመ ሪፖርት ጋር ተናባቢ ሆኖ መቅረብ ያለበት መሆኑንም በትኩረት አይቷል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የቀረበው ሪፖርት በየደረጃው ተገምግሞ የመጣ መሆን እንደሚገባው እና በአሃዛ የተገለፁ ተግባራት ደጋፊ ሰነድ ሊኖራቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ዘርፎች በበጀት ዓመቱ ያከናወኑትን በጥንካሬና በክፍተት ያነሱ ሲሆን መረጃ አደራጅቶ ከመያዝ አንፃር ክፍተቶች መኖራቸውንም ገልፀዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ ዕቅድ የሥራ መመሪያ ሆኖ ከተሰራ ተጠያቂነትን እያሰፈኑ መሄድ ይቻላል ብለዋል፡፡ አያይዘውም ቅሬታ፣ አቤቱታና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ሪፖርት ገላጭና በመረጃ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments