የተቀናጀ የመንግስት ሰራተኞች መረጃ አስተዳደር...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የተቀናጀ የመንግስት ሰራተኞች መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የተቀናጀ የመንግስት ሰራተኞች መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ላይ ስልጠና ተሰጠ፡፡


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም


ኮሚሽኑ ሰራተኞች Integrated Civil Service Management Information System (ICSMIS) በመጠቀም የሚፈልጉትን አስተዳደራዊ ጉዳይ በተለይም የዓመት ፈቃድ መጠየቅ ስለሚችሉበት አግባብ በኢትዮጲያ ሥራ አመራር አካዳሚ ስልጠና ሰጥቷል፡፡


ባለሙያዎቹ ስልጠና መሰጠቱ መልካም መሆኑን አንስተው ከቴክኖሎጂው አቅርቦት አንፃር ደጋግሞ መለማመድና መጠቀም ካልተጀመረ ሊረሳ የሚችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡


አያይዘውም በተለይ በመደበኛ ኢንተርኔት አገልግሎቱን ማግኘት የማይቻል መሆኑ ለልምምድም ሆነ በፈለጉበት ቦታ ሆኖ ለመጠቀም ስለማያስችል የሚመለከተው አካል ሲስተሙ በመደበኛ ኢንተርኔት የሚሰራበትን አግባብ ማመቻቸት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡


እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ ዓለም ከደረሰችበት የቴክኖሎጂ ደረጃ አንፃር ገና ብዙ የሚቀረን ቢሆንም ልምምድ ውስጥ መግባታችን ግን የሚበረታታ መሆኑ ተነስቷል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments