
የእንስሳትን ጤንነት መጠበቅ ከምርት ማሳደግ ባሻገር የሰዎችን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡
የእንስሳትን ጤንነት መጠበቅ ከምርት ማሳደግ ባሻገር የሰዎችን ጤንነት መጠበቅ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የሾላ የእንስሳት ላብራቶሪ ማዕከል የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት የሚጎዱ፣ በዘላቂነት የእንስሳት ጤና ችግር የሆኑና ሞት የሚያስከትሉ፣ ለሰዎች የጤና ችግር መንስኤ የሆኑ እና የሚሆኑ የላብራቶሪ ምርመራዎችን ይሰራል፡፡
ለኢፌዲሪ ግብርና ግብርና ሚኒስቴር፣ ለክልሎችና ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰፊ አገልግሎት የሚሰጥ እንደ ሀገርም ረጅም ጊዜ የቆየ ታሪክ ያለውና ልምድ ለመውሰድም ብዙዎች የሚጠቀሙት ማዕከል መሆኑን የማዕከሉ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪ ቡድን መሪ አቶ ፍስሃ ክንፈ ተናግረዋል፡፡
ቡድን መሪው አያይዘውም የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለተግባራዊ ትምህርት መስክ በሚወጡበት ወቅት ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ወደ ማዕከሉ በመምጣት ልምድ የሚወስዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በቅርቡም የዓለም የምግብ ድርጅት (FAO) ቴክኒክ ቡድን (Dr. Chengerai Njagu Country Team Leader Represenatative in Ethiopia Dr. Esayas Gelaye Vice Director እና Mr. Tenaw AMR Specialized ወደ ማዕከሉ በመምጣት ልምድና ተሞክሮዎችን የወሰዱ መሆኑን አቶ ፍስሃ አንስተዋል፡፡
የላቦራቶሪ ማዕከሉ እንደተመለከትነው የእንሰሳትን ጤና በመጠበቅ ምርት ከማሳደግ ባሻገር ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላልፉ በሽታዎችን በመለየት ቅድመ መከላከል ላይ ሰፊ ሥራ ይሰራል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments