
አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ልማት ዘለቄታዊ ውጤታማነት አለው፡፡
አካል ጉዳተኞችን ያካተተ ልማት ዘለቄታዊ ውጤታማነት አለው፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ለ38 የልማት ተነሺ አካል ጉዳተኛ አርሶ አደሮች የአካል ድጋፍ ድጋፍ አደረገ፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ከተማችን አዲስ አበባ አርሶ አደሩን ማዕከል ያደረገ የልማት ሥራ እየሰራች ሲሆን አርሶ አደሩም ከከተማዋ ልማት ጋር አብሮ እየለማ ይገኛል ብለዋል፡፡
የልማት ተነሺ አርሶ አደሮችን ምንም ገቢ የሌላቸውና መስራት የማይችሉ፣ ገቢ ቢኖራቸውም መስራት የማይችሉ እና መስራት የሚችሉ ብለን በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እያደረግን እንገኛለን በማለት ተናግረዋል፡፡
አክለውም ይህ የተደረገው ድጋፍ በቂ እንዳልሆነና ለተጎጅዎቹ ግን አስፈላጊ በመሆኑ እንደየ አካል ጉዳታችሁ ሁኔታ ታስቦ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የተደረገው ድጋፍ ኮሚሽኑ ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች በተለይም ለአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ብሎ በፕሮጀክት ካቀደው አንዱ ተግባር ሲሆን ሌሎች በርካታ የድጋፍ ዓይነቶችም እየተደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
21 ክራንች፣ 15 ዊልቸር እና ሁለት በትር በጥቅሉ 38 የአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ቁሳቁስ ተገዝቶ ለአካል ጉዳተኞቹ ተበርክቷል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው አካላት በተደረገላቸው ድጋፍ እጅግ በጣም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments