
ቴክኖሎጂ የአገልግሎት ውጤታማነትን ያሳድጋል፡፡
ቴክኖሎጂ የአገልግሎት ውጤታማነትን ያሳድጋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ቴክኖሎጂ ሳይንሳዊ ዕውቀትን ለችግሮች መፍቻ ይውል ዘንድ በቴክኒካዊ ይዘት ወይም ቅርጽ በመፍጠር በኢንዱስትሪዎችና ልዩ ልዩ የልማት ዘርፎች ለተለያዩ ተግባራትና ዓላማዎች ጥቅም ላይ መዋልን የሚያመለክት ጽንሰ-ሃሳብ ነው፡፡
በአሁኑ ዘመን ቴክኖሎጂ ክስተት በሚመስል መልክና በሚያስደንቅ አኳኋን በገፍ በመፈጠርና ጥቅም ላይ በመዋል ላይ ይገኛል፡፡
ቴክኖሎጂን ጥቅም ላይ የማዋል ሂደት ከፍተኛ መሻሻሎችን እያስመዘገበ የመጣ ሂደት ሲሆን ይህ ዕድገት በየዕለቱ የሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ብቻ የሚስተዋል ሳይሆን በሌሎች ዘርፎችም ዘንድ በሰፊው ጥቅም ላይ መዋል ችሏል፡፡
ቴክኖሎጂ በፈርጀ-ብዙ መልኩ ጥቅም ላይ መዋል መቻሉ የሰው ልጅ ስልጣኔንና አኗኗር በሚያስደምም አኳኋን ያሳለጠ ሲሆን በዋናነት በመረጃ አያያዝ፣ በጤና አጠባበቅ፣ ትምህርትና ኮሙዩኒኬሽን ዘርፎች ላይ የመጡ ለውጦችን በማስረጃነት ማንሳት ይቻላል፡፡
ማህበረሰብና ቴክኖሎጂ ላይለያዩ የተጣመሩ በሚመስል መልኩ የተጋመዱ ስለመሆናቸው በርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡
የኢንፎርሜሽን፣ ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ጌቱ በቀለ ኮሚሽኑ ለተገልጋዮች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ አስደግፎ ለመስጠት በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
የአርሶ አደሮችን፣ የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎችን፣ የንብረት አስተዳደር እና የተቀናጀ የመንግስት ሰራተኞች መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ሥራ ላይ ለማዋል በኮሚሽኑ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተሰርተው ወደ ተግባር የተገባ መሆኑንም የቡድን መሪው ጠቅሰዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments