
ሱፐርቪዥን የተቋምን የአፈፃፀም ውጤታማነት ለማሻሻል የሚያገለግል የአሰራር ሥርዓት ነው።
ሱፐርቪዥን የተቋምን የአፈፃፀም ውጤታማነት ለማሻሻል የሚያገለግል የአሰራር ሥርዓት ነው።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
በከተማ ደረጃ የተዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን የማጠቃለያ ምዕራፍ ሥራዎችን ምልከታ እያደረገ ይገኛል።
የሱፐርቪዥን ቡድኑ በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን እና በተጠሪ ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች የማጠቃለያ ምዕራፍ ዕቅድ አፈፃፀም ሱፐር ቪዥን እያካሄደ ይገኛል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የሱፐርቪዥን ቡድን አባላቱን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት በበጀት ዓመቱ የተሰሩ ሥራዎችን ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበዋል።
የክብርት ከንቲባ አማካሪ አቶ ጥላሁን ሮባ በመግቢያቸው ላይ ሱፐርቪዥን የተቋማትን ዕቅድ አፈፃፀም ለማሻሻል የምንጠቀምበት የአሰራር ሥርዓት መሆኑን ገልፀዋል።
የሱፐርቪዥን ቡድን መሪው አቶ ጥላሁን ሮባ የሱፐርቪዥን ቡድኑ ምልከታ የሚያደርግባቸውን የቼክሊስታቸውን ዋና ዋና ነጥቦች አንስተው ቡድኑ የተሰሩ ሥራዎችን ምልከታ እያካሄደ ይገኛል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments