
የሚደልቡ እንስሳት ግዥ ክብደት መለየት ወሳኝ ሙያዊ ተግባር ነው።
የሚደልቡ እንስሳት ግዥ ክብደት መለየት ወሳኝ ሙያዊ ተግባር ነው።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም
በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ውስጥ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የዳልጋ ከብት ማድለብ ይገኝበታል። በዚህ ክላስተር ውስጥ የሚደልቡ እንስሳትን ከመምረጥና በግዢው ከመሳተፍ ጀምሮ ብዙ የክትትልና ድጋፍ ተግባራት በባለሙያዎች ይደረጋሉ።
የሚደልቡ እንስሳት ግዥ ክብደት መለየት ወሳኝ ተግባር ነው። በእንስሳት ማድለብ ሂደት እንስሳቱ ወደ ማድለቢያ ማዕከል ሲገቡ እና ከገቡ በኋላ በሂደት የሚያስመዘግቡትን የክብደት ልዩነት በመከታተል ከዚያም ደልበው ሲወጡ የሚኖራቸውን የክብደት ልዩነት መረጃ በመያዝ ውጤታማነታቸውን መለካት ይገባል፡፡
በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በየጊዜው ተገዝተው ለማድለብ የሚገቡ እንስሳት ክብደት ሲገቡ፣ ከገቡ በኋላ በቆይታቸው በየጊዜው እና ደልበው ሲወጡ የክብደታቸው መጠን ተወስዶ ውጤታማነታቸው ይሰላል።
ይህ ዓይነቱ ተግባር ሙያዊ በሆነ መንገድ የሚከናወን ሲሆን ለአርቢው ለቀጣይ ሥራ የመጀመሪያው አፈፃፀም እንደመነሻ እየተደረገ እንደሚወሰድ የማዕከሉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ፡፡
መረጃውን የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ነው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments