ሱፐርቪዥን የአቅም ግንባታ ሥራ ከሚሰራባቸው ተቋ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ሱፐርቪዥን የአቅም ግንባታ ሥራ ከሚሰራባቸው ተቋማዊ አሰራር ዋነኛው ነው፡፡

ሱፐርቪዥን የአቅም ግንባታ ሥራ ከሚሰራባቸው ተቋማዊ አሰራር ዋነኛው ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 25 ቀን 2017 ዓ.ም



በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተዋቀረ የሱፐርቪዥን ቡድን የኮሚሽኑን የ2017 በጀት ዓመት የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎች በመስክና በዴስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
የሱፐርቪዥን ቡድኑ ለቀናት በመስክና በዴስክ ያደረገውን የሰነድ ፍተሻ እና የመስክ ምልከታ ግብረ-መልስ የኮሚሽኑ ጄነራል ካውንስል በተገኘበት አቅርቧል፡፡
በውይይቱ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የበጀት ዓመቱን ዕቅድ በወቅቱ በጥራት በማቀድ፣ ለሚመለከታቸው አካላት እስከወረዳ ካስኪድ በማድረግ፣ ተወያይቶ የጋራ በማድረግ ሥራዎች እየተሰሩ አፈፃፀማቸው እየተገመገመ የማስተካከያ እርምጃዎች ሲወሰዱ የነበረ መሆኑን አንስተዋል፡፡
አክለውም ሥራዎችን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በመደበኛና በሌማት ትሩፋት የተያዙ ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ ትኩረት በመስጠት ይሰራ እንደነበረ ተናግረዋል፡፡
ኮሚሽኑ በቅንጅታዊ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር ለሚተገበሩ ተግባራትም በተለይ በ2ኛው መንፈቅ ዓመት ልዩ ትኩረት በመስጠትና አሰራር በመዘርጋት ተግባራዊ የተደረገ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የክብርት ከንቲባ አማካሪ አቶ ጥላሁን ሮባ ኮሚሽኑ እጅግ በጣም በርካታ ሰው ተኮር ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን እና ይህንንም በዴስክና በመስክ ማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
የሱፐርቪዥን ቡድኑም በመንግስትና በፓርቲ የተሰሩ ሥራዎች መልካም መሆናቸውን በማንሳት ትኩረት ተሰጥቶ በቀጣይ ቢስተካከል ያሉትንም በቃል ግብረ-መልሳቸው ገልፀዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በጥንካሬ ያነሳቸውን አጠናክሮ በማስቀጠል ክፍተቶችን ደግሞ በማረም በቀጣይ የተሸለ ውጠየት ለማስመዝገብ የዕቅዳችን አካል አድርገን እንሰራለን ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments