የከተማ ግብርና ልማት መጠናከር ጤናማ ትውልድ ለ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የከተማ ግብርና ልማት መጠናከር ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል፡፡


                                                                                                                           ዜና ትንታኔ



የከተማ ግብርና ልማት መጠናከር ጤናማ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል፡፡



አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም



የከተማ ግብርና ልማት መስፋፋትና መጠናከር የግብርና ምርት አቅርቦትን ከገጠር ይጠብቅ የነበረውን ሸማች ከተሜ ወደ አምራችነት የማሸጋገር ሥራ ነው፡፡


የከተማ ግብርና ልማት ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓትን በማሳደግ አምራች ትውልድ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ስላለው ዘርፉን በምርምር ማገዝ ከሁሉም የዘርፉ ባለሙያዎች የሚጠበቅ ተግባር ነው፡፡


የሥነ-ምግብ ባለሙያዎችና ተመራማሪዎች መንግስት በከተማ ግብርና ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱ ማህበረሰቡን በተለያየ መንገድ ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን በተለያዩ መድረኮች ላይ ሲገልፁ ይስተዋላል።


በከተማ በግቢ እና በተክኖሎጂ በመታገዝ በአጥርና በግድግዳ ላይ የሚከናወነው የግብርና ልማት ኢኮኖሚን ከመደገፍ ባለፈ ጤናማ ማህበረሰብ እንዲፈጠር አበርክቶው የጎላ ነው።


የከተማ ግብርና ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓትን በማጎልበት ጤናው የተጠበቀ አምራች ትውልድ እንዲፈጠር የሚያግዝ መሆኑንም ከተማችን ላይ እየሰራን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ መረዳት ይቻላል፡፡


የከተማ ግብርና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባለፈ የአካል እንቅስቃሴ ለማድረግ ዕድል ስለሚፈጥር ጠቀሜታው እጥፍ ድርብ ነው።


በሌላ መልኩ ከተፈጥሮ የተነጠለውን ማህበረሰብ የከተማ ግብርናን በማስፋፋትና በማጠናከር ከተፈጥሮ ጋር ማዛመድ ነው፡፡


አሁን ላይ በከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪው ለከተማ ግብርና የሰጠው ትኩረት ቀላል የማይባል በመሆኑ ልማቱን ውጤታማ እያደረገው ይገኛል፡፡ 


ለዚህም ትልቁ ማሳያ አንዱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆን የከተማ ግብርና ተሳታፊና ተጠቃሚዎች በአሁኑ ወቅት በዘርፉ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡


የመንግስት እና የግል ተቋማትም ቢሆኑ ለከተማ ግብርና ልዩ ትኩረት በመስጠት የምርት ማዕከል እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ በተለይ ትምህርት ቤቶች የሰርቶ ማሳያ ማዕከል እስከመሆን የደረሱ አሉ፡፡


የሚለማው የግብርና ልማትም ተፈጥሯዊ ይዘቱን በጠበቀ መልኩ ስለሆነ ጤናማ ሕይወትን ለመምራት አጋዥ መሆኑን ሁሉም ተጠቃሚና የግብርና ቤተሰብ ያምንበታል።


በከተማ ግብርና ቶሎ የሚደርሱና ለምግብት የሚውሉ የተለያዩ አትክልቶችን እና የእንስሳት ውጤቶችን አልምቶ መጠቀም በስፋት እየተለመደ መምጣጡን ከተማችን ጥሩ ማሳያ መሆን እየቻለች ነው፡፡


የከተማ ግብርና ልማት ከምግብነት ባለፈ የምንኖርበትን አካባቢ አረንጓዴ ስለሚያደርገው ለአዕምሮ ጤናም ጉልህ ድርሻ አለው፡፡


ህብረተሰቡ የከተማ ግበርናን ልማድ አድርጎት እንዲቀጥል ደግሞ ከቴክኖሎጂ አቅርቦት ጀምሮ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና ግንዛቤ የማሳደግ ሥራን ተከታታይነት ባለው መልኩ ማጠናከር የዘርፉ ተግባርና ኃላፊነት ነው፡፡


ለከተማ ግብርና ያገለገሉና የወዳደቁ እቃዎችን በመጠቀም ካሮት፣ ጎመን፣ ቆስጣ፣ ሰላጣ፣ ቃሪያና መሰል አትክልቶችን በማልማት እንዲሁም በትንሽ ቦታ ላይ እንስሳትን በማርባት እንስሳትንና የእንስሳት ውጤትን በመጠቀም ቤተሰብንና አካባቢን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል በተግባር ላይ እየዋለ ያለው የከተማ ግብርና ስራ ጥሩ ማሳያ ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments