
ምክር ቤቱ በከተማ ግብርናና በሌማት ትሩፋት ሥራዎች ተሰማርተው ሞዴል ለሆኑ የምክር ቤት አባላት ዕውቅና ሰጠ።
ምክር ቤቱ በከተማ ግብርናና በሌማት ትሩፋት ሥራዎች ተሰማርተው ሞዴል ለሆኑ የምክር ቤት አባላት ዕውቅና ሰጠ።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 27 ቀን 2017 ዓ.ም
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት በ2017 በጀት ዓመት በከተማ ግብርና እና በሌማት ትሩፋት ስራዎች ላይ ተሰማርተው ሞዴል ለሆኑ የምክር ቤት አባላት እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።
በእውቅና መርሃ-ግብሩ ላይ የክፍለ ከተማው ምክር ቤት አፈ -ጉባዔ አቶ መኩሪያ ጉሩሙ ምክር ቤቶች የህዝብ ሉዓላዊነት መገለጫዎች ናቸው፤ በተለይም የአስፈጻሚውን አካላት በመከታተል ፣ በመቆጣጠርና በመደገፍ የህብረተሰቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲያገኙ፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባራት፣ የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
አፈ- ጉባዔው አክለውም በዛሬው ዕለት የምናከናውነው የዕውቅና ሽልማት ፕሮግራም ከ10ሩም ወረዳ የተወጣጡ የምክር ቤቱ አባላት መካከል በከተማ ግብርና በሌማት ትሩፋት በጓሮ አትክልት ዘርፍ ፣ በዶሮ እርባታ ዘርፍ ፣ በከብት እርባታ ዘርፍ ፣ በንብ ማነብ ዘርፍ ሞዴል የሆኑ ከራሳቸው ፍጆታ አልፈው የኑሮ ውድነቱን ለማረጋጋት ምርቶቻቸውን ወደ ገበያ በማውጣት ገቢ ማግኘት የቻሉና ለሌሎች የስራ ዕድል ዕድል መፍጠር የቻሉ ለዛሬ ዕውቅና ምክር ቤቱ ሰጥቷቸዋል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባዔ ወ/ሮ ይምጡበዝና አረጋኸኝ በበኩላቸው የምክር ቤቱ አባላት በባለፉት ዓመታት ዘርፈ ብዙ ተግባራትን አከናውኗል በተለይም በከተማ ግብርና በሌማት ትሩፋት ውጤት በማምጣት ላይ ይህን ማስቀጠልና ለሌሎች ተሞክሮ በሚሆን መልኩ ማስፋት ያስፈልጋል ብለዋል።
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ ምክር ቤቱ የከተማ ስራዎችን ግብርናና የሌማት ትሩፋት ስራዎች ከመደገፍና ከመከታተል ባሻገር ባለቤት ሆኖ እየሰራ በመሆኑ ምስጋና አቅርበው ምክር ቤቱ ያከናወነው ተግባር ለሌሎች ተቋማት አርዓያ የሚሆን በመሆኑ እንደ ተሞክሮ በመውሰድ በቀጣይ በቅንጅት እንሰራለን ብለዋል።
የምክር ቤት አባላት በጓሮ አትክልት ፣በዶሮ እርባታ ፣ በከብት እርባታና በንብ ማነብ ሞዴል የሆኑ እንዲሁም አስተዋጽዖ ላበረከቱ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላት የዋንጫና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃው የክፍለ ከተማው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments