
ከተማ ግብርና ከተማችን ላይ ባህል እየሆነ ነው።
ከተማ ግብርና ከተማችን ላይ ባህል እየሆነ ነው።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከተማ ግብርና በአምራች እጆች ከተማችን አዲስ አበባ ላይ ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የኮሚሽኑ መዋቅር ከማዕከል እስከ ወረዳ የልማት ተነሽ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋምና የማልማት፣ አርሶ አደሮችን ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ የማድረግ፣ የከተማ ግብርናን የማስፋፋትና የማጠናከር፣ ደህንነቱ፣ ጥራቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የግብርና ምርትና አገልግሎት ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ የማድረግ ሰፊ ሥራ በበጀት ዓመቱ የተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ አርሶ አደሮችን መልሶ ከማቋቋምና በዘላቂነት ከማልማት ጋር በተያያዘ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን የተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
አያይዘውም ከመብት ፈጠራ ጋር ተያይዞ ሰፊ ሥራ እየተሰራ ቢሆንም ከቅንጅታዊ ተቋማት አፈፃፀም ጋር በተያያዘ የተለያዮ ችግሮች መኖራቸውን እና ችግሮቹ እንዲፈቱ ኮሚሽኑ ትኩረት ሰጥቶ በመስራቱ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል።
የከተማ ግብርና ዘርፍ ም/ኮሚሽነር አቶ መለስ አንሼቦ ዕቅድና ሪፖርት ተናቦ እና በየደረጃው ባሉ አደረጃጀቶች ተገምግሞ መቅረብ ያለበት መሆኑን ተናግረዋል።
አክለውም የከተማ ግብርና እየሰፋና እያደገ መምጣት የፍላጎት መጨመርንና ፈታኝ ጉዳዮችን ስለሚፈጥር ስልታዊ ትግል ይጠይቃል ብለዋል።
የክፍለ ከተማና የወረዳ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ቡድን መሪዎች በሥራ ላይ ያስመዘገቡትን ጠንካራ ጎን፣ ክፍተቶች፣ ከቅንጅታዊ ተቋማት የጋራ ሥራ ጋር በተያያዘ የገጠማቸውን ችግር በተለይም ከመብት ፈጠራ ጋር በተያያዘ ያሉ ፈታኝ ጉዳዮችን በዝርዝር አንስተዋል።
አያይዘውም ከአደረጃጀትና ከሰራተኛ ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ በትኩረት ቢሰራ የሚል ሃሳብ አንስተዋል።
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከመብት ፈጠራ ጋር በተያያዘ የተነሳውን ጉዳይ በተመለከተ አሰራርን ተከትሎ መስራት፣ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር ተቀራርቦና ተግባብቶ መስራት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን አምርሮ መታገል ይገባል ብለዋል።
ከተማ ግብርናን ከማስፋፋትና ከማጠናከር ጋር በተያያዘ ሰፊ ሥራ ተሰርቷል፤ በተለይም አርቢዎች በተከታታይ ያነሱት የነበረውን የመኖ ጉዳይ ኮሚሽኑ ችግሩን ለመፍታት ሰፊ ሥራ ሰርቷል፤ ክፍለ ከተማና ወረዳ ደግሞ ይህንን ጉዳይ መሬት ማስነካት ይጠበቅባችኋል ብለዋል።
ከአደረጃጀትና ጥቅማጥቅም ጋር በተያያዘ የተነሱ ሃሳቦችን በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ጥያቄው መልስ የሚያገኝ ይሆናል ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments