የከተማ ግብርና ምርት ገበያ ላይ በስፋት እየቀረ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የከተማ ግብርና ምርት ገበያ ላይ በስፋት እየቀረበ ይገኛል።

የከተማ ግብርና ምርት ገበያ ላይ በስፋት እየቀረበ ይገኛል።


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም


የከተማ ግብርና ምርቶች በኢግዚብሽን ማዕከል በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።

የእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ በዛሬው ዕለት ከ25,000 በላይ እንቁላል ያቀረቡ ተሳታፊ የሆኑ 5 ማህበራት ይዘው መቅረባቸውን ገልፀዋል።

በኢግዚብሽን ማዕከል ተዘዋውረን እንደተመለከትነው እንቁላል 10 ብር፣ ድንች በኪሎ 25 ብር፣ ቲማቲም በኪሎ 35 ብር፣ ጥቅል ጎመን በኪሎ 25 ብር እና ሌሎች ምርቶችም በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።

ኮሚሽኑ እንዲሳተፍ ያደረጋቸው ሦስት ማህበራት በማር፣ ሦስት ማህበራት በአትክልት፣ 5 ማህበራት በእንቁላል ምርታቸውን ይዘው የቀረቡ መሆኑን ተመልክተናል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments