
እንቁላል ለሁሉም በሁሉም።
እንቁላል ለሁሉም በሁሉም።
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
በአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በአዲስ ከተማ፣ በአራዳ፣ ቂርቆስ፣ ልደታ፣ የካ ሴቶች አደባባይ፣ ቦሌ እና በማዕከሉ በ10 ብር ለተጠቃሚዎች እየሸጠ ይገኛል።
የጉለሌ ክፋለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ሰንበት ገበያ ላይ በዛሬው እለት እንቁላል በ14 ብር ለተጠቃሚዎች እየተሸጠ መሆኑን ገልፀውልናል።
አያይዘውም በቂ የእንቁላል ምርት መኖሩን እና ሌሎች የግብርና ምርቶችም በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ በበቂ ሁኔታ መቅረቡን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ በለጠች ተሰማ በርካታ ማህበራት ሰንበት ገበያ ላይ የከተማ ግብርና ምርቶችን ይዘው እየተሳተፉ መሆኑን ገልፀዋል።
እንደ ኃላፊዋ ገለፃ የግብርና ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ እየቀረበ መሆኑን በተለይም እንቁላል በሰንበት ገበያ 14 ብር እየተሸጠ እንደሆነ ተናግረዋል።
እንቁላል ለሁሉም በሁሉም ብለን ከሰራን እንቁላል ላይ የሚታየውን የዋጋ መለዋወጥና ጭማሪ ማረጋጋት እንደሚቻል ያለው ነባራዊ ሁኔታ ገላጭ ነው።
በከተማ ደረጃ ከ98 በላይ በሆኑ የሰንበት ገበያዎች ላይ በበቂ ሁኔታ የከተማ ግብርና ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ ለሸማቹ ማህበረሰብ እየቀረበ ይገኛል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments