
የከተማ ግብርና ምርቶች ከ98 በላይ በሆኑ የሰንበት ገበያዎች ላይ ለሸማጮች እየቀረበ ይገኛል፡፡
የከተማ ግብርና ምርቶች ከ98 በላይ በሆኑ የሰንበት ገበያዎች ላይ ለሸማጮች እየቀረበ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም
በሁሉም ክፍለ ከተማ በሚገኙ የሰንበት ገበያዎች ላይ የከተማ ግብርና ምርቶች በበቂ ሁኔታ ለሸማቹ ማህበረሰብ እየቀረበ ሲሆን እንቁላል ዛሬም 14 ብር መሸጡን እንደቀጠለ ነጠ ይገኛል፡፡
በአርሶ አደርና ከተማ ግበርና ልማት ኮሚሽን የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በአራዳ፣ አዲስ ከተማ፣ ልደታ፣ የካ፣ ቦሌ፣ ቂርቆስና አቃቂ በማዕከሉ እንቁላል በ10 ብር እየተሸጠ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ እንቁላልን በ10 ብር ከማዕከሉ ውጭ በየክፍለ ከተማው የመሸጫ ሱቅ ከፍቶ እየሸጠ መሆኑ ዋጋን ከማረጋጋት ባለፈ ዋጋን እስከመተመን ደርሷል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ በማህበራዊ ድህረ-ገፃችን ላይ እንዳጋሩን ከሆነ በዛሬው ዕለት የእንቁላል ምርት በሰንበት ገበያ ላይ በበቂ ሁኔታ ለሸማቹ መቅረቡን አንስተዋል፡፡
የከተማ ግብርና ምርቶች በበቂ ሁኔታ ገበያ ላይ በተለይም ከ98 በላይ በሆኑ የሰንበት ገበያዎች ላይ መቅረቡ የዋጋ ማረጋጋትን እየፈጠረ እንደሆነ ሸማጮችም ሃሳብ እየሰጡ ይገኛል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments