
የንቅናቄ ስራዎች የላቀ ድል ለማስመዝገብ ማስፈንጠሪያዎች በመሆናቸው በልዩ ትኩረት ሊከወኑ ይገባል !
የንቅናቄ ስራዎች የላቀ ድል ለማስመዝገብ ማስፈንጠሪያዎች በመሆናቸው በልዩ ትኩረት ሊከወኑ ይገባል !
በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በሌማት ቱሩፋት እና ልመናንና ተረጅነትን ከማስቀረት አኳያ ባለፈው ሳምንት በየክ/ከተማው የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም የጋራ ያደረጉ ሲሆን፤ በንቅናቄው ጅምር እንቅስቃሴዎች ላይ የነበሩ ጉድለቶች እንዲታረሙ ፣ ጥንካሬዎች ደግሞ እንዲጎለብቱ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ ባስተላለፉት መልዕክት የስራ ዕድል ፈጠራ ፣ የሌማት ቱሩፋት እና ሌሎችም የንቅናቄ ስራዎች በቅርቡ በከተማ አቀፍ ግብረ ሀይሉ መገምገማቸውን አስታውሰው ጊዜና ጉልበትን በሚቆጥብ መልኩ በዛሬው ዕለት የተጀመረው በቴክኖሎጂ የታገዘ የግንኙነት አግባብም ስራዎችን ከስር ከስር እየገመገሙ ለመሄድ እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
አመራሩ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን ስለሚመራ ስራዎች እንዳይንጠባጠቡ ማቀናጀትና በሱፐርቪዥን ማስደገፍ እንደሚገባው ያሳሰቡት አቶ ሞገስ በፓርቲያችንም ቀይ መስመር ተብሎ የተቀመጠውን የሀሰት ሪፖርት ፣ እንደ ቆሻሻ የመፀየፍ ባህልን ማጎልበት እንደሚገባም በአፅንዖት ገልፀዋል።
የሌማት ቱሩፋት ስራዎች በገበያ ማረጋጋቱ ላይም ትርጉም ያለው ውጤት ሊያመጡ ስለሚገባ በተለይም ለዘርፉ ዕምቅ አቅም ያላቸው የማስፋፊያ ክ/ከተሞች አንፀባራቂ ድል ለማስመዝገብ በልዩ ትኩረት ሊረባረቡ እንደሚገባ አቶ ሞገስ አስገንዝበዋል።
በየደረጃው የሚገኙ የፓርቲ እና የክንፎች አመራሮች ፣ የወጣቶችና ስፖርት እንዲሁም የሴቶች ፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ አመራሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ርብርብን ማጠናከር እንደሚገባቸው የጠቆሙት አቶ ሞገስ ለንቅናቄ ስራዎች የተቋቋሙ ግብረ ሀይሎችም የሚጠበቅባቸውን ሊወጡ እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ በባለፉት ዓመታት በሌማት ትሩፋት የተመዘገበው ውጤት ቀላል የማይባል መሆኑን ገልፀዋል።
አያይዘውም የሌማት ትሩፋት ለብዙዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እያገዘ ያለ፣ ለገበያ መረጋጋት ከፍተኛ ሚና ያለው፣ መደበኛውን የግብርና ሥራ ያቀላጠፈና በተለይ በእንስሳት ሃብት ልማት ትልቅ ውጤት የተመዘገበበት የንቅናቄ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments