
በ2016/17 ምርት ዘመን ከነበረው 18,608 ቶን የሰብል ምርት ግምት በ2017/18 ምርት ዘመን ወደ 19,361.73 ቶን እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
በ2016/17 ምርት ዘመን ከነበረው 18,608 ቶን የሰብል ምርት ግምት በ2017/18 ምርት ዘመን ወደ 19,361.73 ቶን እንዲያድግ ይደረጋል፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 02 ቀን 2017 ዓ.ም
በ2017/18 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ የሰብል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በርካታ ሥራዎች በተለይ በማስፋፊያ ክፍለ ከተሞች ላይ እየተከናወኑ ይገኛል፡፡
ዘመናዊ የሰብል ልማት አሰራር (ኤክስቴንሽን)፣ አመራረት ዘዴ እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም በግልና በተደራጀ (በኩታ ገጠም) አግባብ በመስራት የዘርፉን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንዲቻል ተግባሩ በባለሙያ መደገፍ አለበት፡፡
በ2017/18 ምርት ዘመን 7,165.06 ሄክታር መሬት በዘር ይሸፈናል ተብሎ የታቀደ ሲሆን 19,361.73 ቶን ምርት እንደሚገኝ ግምት የተወሰደ መሆኑን ከፍተኛ የእጽዋት ሃብት ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያም ገልፀዋል፡፡
የ2016/17 ምርት ዘመን ምርታማነት 25.9ኩ/ሄክታር እንደነበር እና በ2017/18 ምርት ዘመን 27ኩ/ሄክታር እንደሚያድግ ባለሙያው ተናግረዋል፡፡
አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያም እስካሁን 50 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን፣ 144.805 ኩንታል ምርጥ ዘር እና 2,421 UREA፣ 2,630 NPS በድምሩ 5,051 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ መሰራጨቱን ገልፀዋል፡፡
የኮሙዩኒኬሽን ሥራ ክፍል የመኸር እርሻ ሥራ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በማስፋፊያ ክፍለ ከተሞች ላይ ምን እንደሚመስል መረጃ የወሰደ ሲሆን እስካሁን ያለው የዝናቡ ሁኔታ ለሰብል ልማት አመች መሆኑን እና በአብዛኛው ቦታ እጅግ በጣም ጥሩ የሚባል አፈፃፀም መኖሩን ተረድተናል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments