ማገልገል ክብር ነው፡፡

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ማገልገል ክብር ነው፡፡

ማገልገል ክብር ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 02 ቀን 2017 ዓ.ም


እኔ ለምሰራበት ተቋም ወሳኝ ሰው ነኝ!፡፡ ለመልካም አገልግሎት አሰጣጥ መልካም አገልጋይነትና መልካም ተገልጋይነት ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡


የአገልግሎት አሰጣጥ እና የተገልጋይ (የደንበኛ) ጽንሰ-ሃሣብ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥራ አመራር፣ ውጤታማ የደንበኛ አገልግሎት ለአንድ ተቋም ህልውና እንደመሠረታዊ ነገር ይቆጠራል፡፡


ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ጥራት ያለው የደንበኛ አገልግሎት አሰጣጥና አያያዝ የአንድ ሰሞን ሥራ ብቻ አለመሆኑን እና የባለጉዳይ (የደንበኛ) አያያዝ የማያቋርጥ ሂደት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡


ዛሬ ሐምሌ 02 ቀን 2017 ዓ.ም አገልግሎት ፈልገው ወደ ኮሚሽኑ ከመጡ ተገልጋዮች መካከል የተወሰኑትን ያነጋገርን ሲሆን በሁሉም አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ተገልጋዩን ቅር ያላሰኘ በጣም ጥሩ መስተንግዶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ተገልጋዮች በርካታ ጉዳዮችን ይዘው ይመጣሉ፤ ይዘውት የመጡት ጉዳይ ሁሉ እኛን ይመለከታል ማለት አይደለም፤ ነገር ግን አገልግሎት ፈልጎ የመጣውን ተገልጋይ ሁሉ በጥበብ ማስተናገድ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡


አንዳንዶቹ ተገልጋዮች ጉዳያቸው በወረዳና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚያልቅ ቢሆንም ከመስተንግዶ ጉድለት የተነሳ ወደ ማዕከል እንደመጡና ተገቢውን አገልግሎት አግኝተው እንደተመለሱ ተናግረዋል፡፡


ሌላው አገልግሎት እየሰጡ ያገኘናቸው የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሣ ተገልጋዮች ከመብት ፈጠራ፣ ከጋራ መኖሪያ ቤት፣ ከመልሶ ማቋቋም፣ ከመስሪያ ካፒታል አለመለቀቅ፣ ከመስሪያ ቦታና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ አገልግሎት ፈልገው እንደመጡ ገልፀውልናል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments