
ቅንጅታዊ ትስስር ለኮሚሽናችን ተልዕኮ መሳካት ስትንፋስ ነው። ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ
ቅንጅታዊ ትስስር ለኮሚሽናችን ተልዕኮ መሳካት ስትንፋስ ነው። ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም
ቅንጅታዊ ትስስር የተቋምን ተልዕኮ ውጤታማ ለማድረግ ከምንጠቀምባቸው ስትራቴጄዊ አሰራሮች አንዱ ነው።
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን በበጀት ዓመቱ ከተፈራረማቸው ቅንጅታዊ ተቋማት ጋር የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አድርጓል።
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ በትስስር ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር በርካታ ሥራዎች መሰራታቸውን በዝርዝር በማንሳት ሃሳብ ሰጥተዋል።
አያይዘውም ኮሚሽኑ በራሱ ጀምሮ በራሱ የማይጨርሳቸው የሌሎች ተቋማትን ከፍተኛ ሚና የሚጠይቁ ተግባራት ያሉት መሆኑን አንስተዋል።
ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ አክለውም አንዳንዶቹ ትስስር የተደረገባቸው ተግባራት ለተቋማቱ ዋና ተግባር ሊሆን ስለሚችል ከተፈፃሚነት አንፃር የትስስር ተቋማት ሚናቸው ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ትስስር የተደረገላቸው ተቋማት በትስስሩ የተሰሩ ሥራዎችን ጥንካሬዎች፣ ክፍተቶች፣ አሰቻይ እና ፈታኝ የነበሩ ጉዳዮችን በዝርዝር አንስተው የጋራ ተደርገዋል።
ወ/ሮ ሎኮ ቅንጅታዊ ትስስር ለኮሚሽኑ ዕቅድ መሳካት ስትንፋስ መሆኑን ገልፀዋል። በበጀት ዓመቱም ከመብት ፈጠራ፣ አርሶ አደሮችን መልሶ ከማቋቋምና ከማልማት፣ የጋራ መኖሪያ ቤት የንግድ ሱቅ ከማስተላለፍ፣ ህገወጥ የእንስሳት እርድና ሥጋ ዝውውርን ከመቆጣጣር ጋር እና በሌሎቹም ጉዳዮች ላይ ሰፊ ሥራ መሰራቱን ገልፀዋል።
አያይዘውም በቀጣይ የ2018 በጀት ዓመት ከባለፈው በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በመነሳት የተሻለ ሥራ ለመስራት ቀድመን ትስስር የምናደርግባቸውን ጉዳዮች በአግባቡ ለይተን የጋራ ማድረግ ስላለብን ሁላችንም በቂ ዝግጅት እንድናደርግ ማሳሰብ እወዳለሁ ብለዋል።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments