
የከተማ ግብርናን ለማስፋት ፣ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ከማሳደግ አኳያ
የከተማ ግብርናን ለማስፋት ፣ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ከማሳደግ አኳያ
👉ማህበረሰቡ በከተማ ግብርና ልማት ስራ ላይ ያለው ግንዛቤ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመሆኑ፤ የተሳታፊዎች ቁጥር እና የከተማ ግብርና ምርት አድጓል፡፡
👉ለአብነት ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት አመት አንፃር ሲነፃፀር ከ171,869 ቶን ምርት በዚህ ዓመት 280,406 ቶን ምርት ማድረስ ተችሏል፡፡
👉2,188 አርሶ አደሮች ከግል ይዞታቸው (ከ20% እስከ 80%) በከተማ ግብርና ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል።
👉አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ከ81 አርሶ አደሮች ውስጥ የ37 አርሶ አደሮች ፕሮጀክቶች የፀደቀ እና ሌሎች ሂደት ላይ ናቸው፡፡
👉የአርሶ አደር የይዞታ መጠቀሚያ መብት ፈጠራ ስራዎችን እንዲጠናቀቅ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር እየተሰራ ሲሆን በዚህም 6,180 ካርታ የታተመ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 4,217 ካርታ ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል፡፡
👉ቀሪዎችንም በቅርብ ጊዜ ውስጥ ስራው ተጠናቆ ለአርሶ አደሩ እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments