እንቁላል የቅንጦት ምግብ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግ...

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

እንቁላል የቅንጦት ምግብ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ አካል ነው፡፡

እንቁላል የቅንጦት ምግብ ሳይሆን የተመጣጠነ ምግብ አካል ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 07 ቀን 2017 ዓ.ም


የእንቁላል ምርት በሁሉም ክፍለ ከተሞች በቅዳሜና እሑድ ገበያ በስፋት የቀረበ መሆኑን ከየክፍለ ከተማው የደረሰን መረጃዎ ያመለክታል፡፡


ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በክፍለ ከተማው በሁሉም ወረዳዎች ላይ በሰንበት ገበያ እንቁላል በአሥራ አራት (14) ብር እየተሸጠ እንደነበር መረጃውን በስልክና በቴሌግራም ነግረውናል፡፡


የጽ/ቤት ኃላፊዋ አያይዘውም ከእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል በትስስር የመጣው እንቁላል ደግሞ በተዘጋጀለት ሱቆች በአሥር (10) ብር እየተሸጠ እንደሆነ ገልፀውልናል፡፡


በሌላ በኩል አቃቂ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 በተዘጋጀ ባዛር ላይ የእንቁላል ምርት አቅርቦት በበቂ ሁኔታ እንደነበረ አቶ ጉደታ ሽብሩ መረጃውን በትስስር ገፃችን ላይ አጋርተውናል፡፡


በአሁኑ ወቅት ገበያ ላይ የእንቁላል ምርት አቅርቦት ችግር እንደሌለ በሰንበት ገበያና በዛሮች ላይ እየቀረበ ያለው የምርት መጠን ማሳያ ነው፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments