
አረንጓዴ ሣር እና ቅጠላቅጠልን ለእንስሳት መመገብ ሊለመድ የሚገባው ተግባር ነው።
አረንጓዴ ሣር እና ቅጠላቅጠልን ለእንስሳት መመገብ ሊለመድ የሚገባው ተግባር ነው።
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 7 ቀን 2017 ዓ.ም
እርጥብ አረንጓዴ ሣር እና ቅጠላቅጠልን ለእንስሳት መመገብ ለእርባታው ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ባለሙያዎች ያነሳሉ።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ በአካባቢያችን የሚገኝ አረንጓዴ እርጥብ ሣር እና ቅጠላቅጠልን ለእንስሳት መመገብ የመኖ ወጭን ከመቀነስ ባለፈ ለእንስሳቱ የንጥረ ምግብ ፍጆታ መጨመር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።
በእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል የእንስሳት መኖ ልማት ባለሙያ አቶ ጌታቸው ገመቹ አረንጓዴ ሣር እና ቅጠላቅጠልን በተለይም ለወተት ከብቶች መመገብ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ዓይነተኛ ሚና እንዳለው ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ አረንጓዴ ሣር እና ቅጠላቅጠል በብዛት የሚገኝበት ወቅት በመሆኑ አርቢዎች በተለይም የወተት ከብት እርባታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ቢጠቀሙበት ውጤታማ እንደሚሆኑ ባለሙያው ጠቁመዋል።
ምንጭ፦ የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments