የቴክኖሎጂ ሽግግር ለከተማ ግብርና ሥራ ወሳኝ ም...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የቴክኖሎጂ ሽግግር ለከተማ ግብርና ሥራ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡


ዜና ትንታኔ


የቴክኖሎጂ ሽግግር ለከተማ ግብርና ሥራ ወሳኝ ምዕራፍ ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም


ግብርና የኢትዮጵያዊያን የዕለት ጉርስ መገኛ፣ የገቢ ምንጭ፣ የአገሪቷ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት፣ ለአብዛኛው የአገሪቷ ህዝብ የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ እድገት ምጣኔ ቀዳሚ ደረጃ ላይ የተቀመጠና የውጭ ምንዛሪ የሚገኝበት ነው፡፡
ባህላዊ (Traditional) የአመራረት ዘዴ ምርታማነቱን በእጅጉ ስለጎዳው አገሪቷ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓታል የሚሉ በርካታ የዘርፉ ምሁራን አሉ፡፡ 


የግብርናውን ዘርፍ በዘመናዊ መንገድ መተግበር ከተቻለ ገበያ ላይ ተፈላጊ የሆኑ የግብርና ምርቶችን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባሻገር የውጭ ገበያን ታሳቢ ያደረገ አመርቂ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ይቻላል።


የግብርና ዘርፈ ብዙ የሆነ ሚና ያለው እና በቦታ የማይገደብ በመሆኑ ከተለምዶው እሳቤና ትግበራ በመውጣት ገጠር ላይ ይተገበር የነበረውን ከተማም ውስጥ በስፋት እና በጥልቀት ተግባራው ማድረግ ግድ ይላል፡፡


የከተማ ግብርና ማለት አነስተኛ በሆነ ቦታ ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእንስሳት (ዶሮ፣ ወተት፣ ንብ፣ ዓሣ፣ ማድለብ፣…)፤ የእፀዋት (አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ የተፈጥሮ ሃብት፣…) ልማት በማካሄድ ማምረት፣ የተመረቱ ምርቶችን ማቀነባበር፣ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እና ምርቱን ለቤት ፍጆታ ከማዋል ባሻገር ለገበያ በማዋል ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መፍጠር ነው።


የዓለም ህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የከተሜነት መስፋፋት፣ የኑሮ ውድነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ መምጣት፣ በከተማ ደረጃ የግብርና ምርት አቅርቦት ፍላጎት መጨመር፣ የአካባቢና የአየር ንብረት ተፅዕኖች እየተባባሱ መምጣት ግብርና በከተማ ውስጥ እንዲተገበር የግድ ብሏል፡፡


በአነስተኛ ወጪ ትኩስ፣ ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ ለማግኘት፤ ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመፍጠር፣ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ አቅም ለማሳደግ፣ ለሴቶች፣ ወጣቶችና አረጋውያን የሥራ እድል ለመፍጠር ከተማ ግብርና ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡


በሌላ በኩል ከተማ ግብርና የመኖሪያ ግቢን እንዲሁም የአካባቢ ውበትን በመጠበቅ ሰዎች የእለት ተእለት ስራቸውን እና ውሎዋቸውን በተነቃቃ መንፈስ እንዲያሳልፉ ለማድረግ፣ የአረንጉዴ ሽፋንን ከፍ በማድረግ በከተማ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን እንዲቀንስ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላል፡፡ እየቻለም ነው፡፡


ከተማ ላይ የማይተገበር የግብርና ዓይነት የለም፡፡ የእንስሳት እርባታ፣ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሰብል፣ እንጉዳይ ምርት እና የቅመማ ቅመም ምርት በአብዛኛው የተለመዱ ናቸው፡፡


በሽቅብ እርሻ፣ አኳ ፎኒክ፣ ኤሮ ፎኒክ፣ ሃይድሮ ፎኒክ፣ ጣራ ላይ፣ ግድግዳ ላይ፣ በረንዳ ላይ እንዲም አትክልትን በማንኛውም አፈር መያዝ በሚችል አሮጌ እቃ (በጆንያ፣ በርሜል፣ ጎማ፣ ማሰሮ፣ ገንዳ፣ ፌስታል፣ ጠርሙስና በመሳሰሉት) ማልማት ይቻላል፡፡ ተችሏልም፡፡


ዶሮን በዘመናዊ ኬጂ፣ የወተት ላሞችን እና ማድለብን በዘመናዊ ሸድ፣ ንብን በዘመናዊ ቀፎ በቤት ጣራና ግድግዳ ላይ በቀላሉ በቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡ አዲስ አበባ ይህን ተግባር በስፋት እየሰራችበት ትገኛለች፡፡


የከተማ ግብርና ሥራ ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ስራ ብቻ ሳይሆን አስደሳችም በመሆኑ የመሬት ችግር ባለበት ቦታ እቃዎችን በመጠቀም አትክልቶችን ማልማት ልምድ መሆን አለበት፡፡ እየሆነም ነው፡፡


ኑ! አብረን እንስራ፤ የምግብ ዋስትናችንን እናረጋግጥ፤ ትኩስ፣ ጤናማና የተመጣጠነ ምግብ ከደጃችን አምርተን እንጠቀም፡፡ ከሸማችነት ወደ አምራችነት እንሸጋገር፡፡


ከየክፍለ ከተሞቹ የተወሰዱ ተያያዥ ምስሎችን ለማስረጃነት መመልከት ይቻላል፡፡
ለበለጠ መረጃ የሚከተሉትን አድራሻዎቻችንን ተከታተሉ፡፡


YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT 
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o



Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments