ስለከተማ ግብርና ምን ያህል ያውቃሉ?

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ስለከተማ ግብርና ምን ያህል ያውቃሉ?


ዜና ትንታኔ


ስለከተማ ግብርና ምን ያህል ያውቃሉ?


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም


የከተማ ግብርና ማለት እጅግ በጣም አነስተኛ በሆኑ ቦታዎች ላይ ወይንም በቤት ግድግዳ፣ ጣራና አጥር ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእንስሳት (የዶሮ፣ ወተት፣ ዓሣና ማድለብ) የእፀዋት (አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የተፈጥሮ ሃብት) ልማት በማካሄድ ማምረትና የተመረቱ ምርቶችን እሴት ጨምሮ ማቀነባበር እና በማከፋፈል ምርቱን ለቤት ፍጆታ ከማዋል ባሻገር ለሽያጭ በማዋል ተጨማሪ የገቢ ምንጭ መፍጠር ነው።
የግብርና ምርትና ምርታማነት በመጠንና በጥራት በማሳደግ ኢኮኖሚን በማሻሻል በከተማና በከተማ ዙሪያ የሚኖረውን ህብረተሰብ የሥርዓተ-ምግብና የምግብ ዋስትና እንዲሻሻል የሚያደርግ እሳቤ ነው፡፡
የከተማ ግብርና ለምን አስፈለገ?
 የዓለም ህዝብ ቁጥር መጨመር፤
 የከተሜነት መስፋፋት፤
 የአካባቢና የአየር ንብረት ተፅዕኖች እየተባባሱ መምጣት፤
#በኢትዮጵያ፡-
 ከ100ሚሊዮን በላይ ህዝብ መድረሱ፤
 ከፍተኛ ህዝብ ከገጠር ወደ ከተማ መፍለሱ፤
 ከተሞች ላይ የግብርና ምርት ዋጋ መናር፤
 አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣም፤ 
#የከተማ ግብርና ጥቅም
 ቤተሰብ በአነስተኛ ወጪ ትኩስ ጤናማና የተመጣጠነ የአትክልት ምግቦችን እንዲመገብ እና ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ እንዲፈጠር ያደርጋል፤
 የሴቶች ኢኮኖሚያዊ አቅም እንዲያድግና በራስ መተማመን እንዲጎለብት ያደርጋል፤
 ለሴቶች፣ ወጣቶችና አረጋውያን የሥራ እድል እንዲፈጠር ያረጋል፤
 የመኖሪያ ግቢን እንዲሁም የአካባቢ ውበትን በመጠበቅ ሰዎች የእለት ተእለት ስራቸውን እና ውሎዋቸውን በተነቃቃ መንፈስ እንዲያሳልፉ ያስችላል፤
 የአረንጉዴ ሽፋንን ከፍ በማድረግ በከተማ የሚስተዋለውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን እንዲቀንስ ጉልህ አስተዋጽኦ ማድረግ ይችላል፤
 በከተሞች የሥራ አጥነትን ይቀንሳል፤
 በከተሞች የሚፈጠረውን የአቅርቦት ውስንነትና የዋጋ ውድነትን ያረጋጋል፤
 የቤተሰብ ተጨማሪ የገቢ ምንጭን በማሳደግ የተሻለ ኑሮ እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡
#የከተማ ግብርና አይነቶች:-
የእንስሳት እርባታ (ዶሮ፣ የወተት ላም፣ ማድለብ፣ ንብ ማነብ፣ አሣ፣ አሳማ፣ ወዘተ)፣ እጽዋት (አትክልትና ፍራፍሬ፣ ሰብል፣ እንጉዳይ ምርት እና የቅመማ ቅመም) ምርት ተጠቃሾች ናቸው፡፡
በቤት ጣራ፣ ግድግዳና አጥር ላይ እንዲሁም በእቃ ላይ አትክልት የማምረት ዘዴ በከተማ ውስጥ የቤተሰብ ፍጆታን ለመሸፈን የሚያስችል፣ የነፍስ ወከፍ ገቢን የሚያስገኝ፣ የቤተሰብ ገቢ (family business) ማስገኛ ግብርና ነው፡፡ 
በሌላ በኩል ደግሞ ትኩስ አትክልት በተለይም የቅጠላ ቅጠል አትክልት ለማግኘት ዋነኛው አማራጭ የተገኘውን ቦታ ተጠቅሞ አትክልት ማምረት ነው፡፡
ስለዚህ አትክልትን በማንኛውም አፈር መያዝ በሚችል አሮጌ እቃ (በጆንያ፣ በርሜል፣ ጎማ፣ ማሰሮ፣ ገንዳ፣ ፌስታል፣ ጠርሙስና በመሳሰሉት) ማልማት ጥሩ ውጤት የሚያስገኝ ስራ ብቻ ሳይሆን አስደሳችም በመሆኑ የመሬት ችግር ባለበት ቦታ እቃዎችን በመጠቀም አትክልቶችን ማልማት ልምድ እየተስፋፋ ነው፡፡
ጣራ ላይ፣ ግድግዳ ላይ እና የሽቅብ/ተንጠልጣይ እርሻ ጠቀሜታ መሬት ቆጣቢ መሆኑ፡- ትንሽ መሬት መነሻ (Ground Base) ቦታን በአየር ላይ መጠቀም መቻሉ፡፡
የአካባቢ ሥነ-ምህዳርን የመጠበቅ ጠቀሜታ፡- በተለይ የተጣሉ ፕላስቲኮችን መጠቀም መቻሉ፡፡
አፈር አልባ በሆነ መንገድ አኳ ፎኒክ፣ ኤሮ ፎኒክ፣ ሃይድሮ ፎኒክ የሚባሉ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ የእጽዋት ልማት ማልማት መቻሉ ሌላኛው ፀጋ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 


YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT 
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


 


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments