ቴክኖሎጂ መር የሆነ የእርሻ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ቴክኖሎጂ መር የሆነ የእርሻ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡

ቴክኖሎጂ መር የሆነ የእርሻ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም



እስካሁን በከተማችን አዲስ አበባ 767.8 ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን ቀሪውን በዘር ያልተሸፈነ በመኸር ሰብል መሸፈን ያለበት መሬት በዘር ለመሸፈን አርሶ አደሩ እየሰራ ይገኛል፡፡
በመኸር የሰብል እርሻ እንቅስቃሴ ክትትል መሰረት እስካአሁን ድርስ የተሰረጨ ማዳበሪያ ዳፕ እቅድ 7,704 ኩንታል ለማሰራጭት ታቅዶ 3525(45.7%) እንዲሁም ዩሪያ 7,704 ኩንታል ለማሰራጭት ታቅዶ 3,327.5(43.19%) በአጠቃላይ በድምሩ የተሰራጨ የአፈር ማዳበሪያ  በኩንታል 6,876.5(44.6%) መሆኑን የእጽዋት ግብዓትና ቴክኖሎጂ አቅርቦት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዮሴፍ ደግፈኝ ገልፀዋል፡፡
ከፍተኛ የእጽዋት ሃብት ልማት ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያም በበኩላቸው ምርጥ ዘር እቅድ 1,065 ኩንታል ሲሆን እስካአሁን የተሰራጨ 144.8 ኩንታል መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 
በሌላ በኩል እንደ ባለሙያው ገለፃ አርሶ አደሮች በራሳቸው አበጥረው ከተጠቀሰው ምርጥ ዘር በተጨማሪ 633.06 ኩንታል ምርጥ ዘር ጥቅም ላይ ያዋሉ በሆኑን ገልፀዋል፡፡
አቶ ዮሴፍ ደግፈኝ እና አቶ ተስፋዬ ኪ/ማርያም የግብዓት አቅርቦት እና የባለሙያዎች ድጋፍና ክትትል ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን አንስተዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments