ቴክኖሎጂን የማላመድ ልምምዱ በየክፍለ ከተማው ት...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ቴክኖሎጂን የማላመድ ልምምዱ በየክፍለ ከተማው ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡

ቴክኖሎጂን የማላመድ ልምምዱ በየክፍለ ከተማው ትኩረት በመስጠት እየተሰራ ይገኛል፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12 ቀን 2017 ዓ.ም



አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማላመድ እና ማህበረሰቡ በቀላሉ ከአፈር ውጭ (አፈር አልባ) በሆነ መንገድ የግብርና ምርት ማምረት እንዲችል ለማድረግ በየክፍለ ከተማው ሰፊ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ኮልፌና ቄርቆስ ክፍለ ከተማ ሰሞኑን እያጋሩን ያለው መረጃ ለዚህ ጥሩ ማሳያ መሆን ይችላል፡፡
ግብርና በተለይም ደግሞ ከተማ ግብርና በቴክኖሎጂ በስፋት እየታገዘ ከመጣ ምርትና ምርታማነት በእጅጉ ከፍ ስለሚል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ ውጠየታማ መሆን ይችላል፡፡
በቴክኖሎጂ የታገዘ የከተማ ግብርና ሥራ በከተማ ውስጥ የሚታየውን የግብርና ምርት አቅርቦት ችግር በመፍታት ዋጋን ከማረጋጋት ባለፈ የማይተካ ኢኮኖሚያዊ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አዳዲስ አሰራሮች፣ ቴክኖሎጂዎች እና ምርጥ ተሞክሮዎች እየተቀመሩ መስፋትና መላመድ እንዲችሉ ሁሉም የግብርና ቤተሰብ የበኩሉን ማበርከት ይጠበቅበታል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments