ፕሬስ ሪሊዝ

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ፕሬስ ሪሊዝ


ፕሬስ ሪሊዝ


የአርሶ አደር እና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በከተማችን የከተማ ግብርናን በከተማው የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ ሂደት ድርሻውን ከማሳደግ አንጻር በመደበኛና በንቅናቄ ሰፋፊ ስራዎች በመስራት ማጠናከር የተቻለ ሲሆን በተለይም የሌማት ቱሩፋት ንቅናቄ ስራ ከተጀመረ በኋላ በርካታ ተግባራት በማከናወን አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ 

የከተማው ማህበረሰብ በከተማ ግብርና ልማት ስራ ላይ ያለው ግንዛቤ ጨምሯል፤ የተሳታፊ ቁጥር እና የከተማ ግብርና ምርት አድጓል፤ የእንቁላል ምርት፣ የወተት ምርት፣ የማር ምርት፣ የአሳ ምርት እና የግቢና ጓሮ አትክልት ልማት ምርት እየጨመረ መምጣቱ ለአብነት ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት አመት አንፃር ሲነፃፀር ከ197,469 ቶን ምርት ወደ 280,406 ቶን ምርት በዚህ በጀት ዓመት ማድረስ ተችሏል፡፡

በዘርፉ 1,028,253 የከተማው ማህበረሰብ እና 2,565 ተቋማት በከተማ ግብርና እንዲሳተፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ 

በመኸር እና በመስኖ ልማት 7,165 ሄ/ር መሬት ማልማት የተቻለ ሲሆን የከተማ ግብርና ተጠቃሚዎች የቤተሰባቸውን ፍጆታ በራሳቸው ከመሸፈን ባለፈ ገቢያቸውን የሚደጉሙበት ሁኔታ የተፈጠረና በከተማው የዋጋ ማረጋገት ሂደት ላይ ጉልህ ድርሻ እያበረከተ ሲሆን የከተማ ግብርና በከተማው ባህል እየሆነ መጥቷል፡፡ 

ጤንነቱና ደህነነቱ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን በቄራ ውስጥ ለ357,902 እንስሳት የቅድመ እና ድህረ እርድ ምርመራ አገልግሎት ከመስጠት በተጨማሪ ህገ-ወጥ የእንስሳት ዕርድና ሥጋ ዝውውር በሚካሄድባቸው 350 ቦታዎች ላይ በቅንጅታዊ ኦፕሬሽን የእርምት እርምጃ የተወሰደ ሲሆን በከተማ ግብርና ንግድና አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ 2,219 ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ 

በልማት ምክንያት ከይዞታቸው የተነሱ አርሶ አደሮችን መልሶ በማቋቋም ለ156 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የብር 41,740,000.00 በብድርና የቀጥታ ፋይናንስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡ መስራት ለማይችሉ 1,089 የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ብር 36,326,102.00 የመሰረታዊ ፍጆታና መጠለያ ቀጥታ ድጋፍ ማድረግ ተችሏል፡፡ 

2,188 አርሶ አደሮች ከግል ይዞታቸው (ከ20% እስከ 80%) በከተማ ግብርና ስራ ወደ ስራ ማስገባት ተችሏል፤ አርሶ አደሮች ወደ ኢንቨስትመንት እንዲገቡ ድጋፍና ክትትል በማድረግ ከ81 አርሶ አደሮች ውስጥ የ37 አርሶ አደሮች ፕሮጀክቶች የፀደቀ እና ሌሎች ሂደት ላይ ናቸው፡፡ 

የአርሶ አደር የይዞታ መጠቀሚያ መብት ፈጠራ ስራዎችን በተመለከተም እንዲጠናቀቅ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር እጅግ በጣም ሰፊ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments