"ከሸማችነት ወደ አምራችነት!" በሚል መሪ ሀሳብ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

"ከሸማችነት ወደ አምራችነት!" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 በጀት ዓመት የመኸር እርሻ ተጠናክሮ እየተካሄደ ነው።

"ከሸማችነት ወደ አምራችነት!" በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 በጀት ዓመት የመኸር እርሻ ተጠናክሮ እየተካሄደ ነው።


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17 ቀን 2017 ዓ.ም


563 አርሶ አደሮች 1,090 ሄክታር ማሳ በመኸር ሰብል ለመሸፈን ሙሉ ዝግጅት ያጠናቀቁ መሆኑን ዛሬ የመኸር እርሻ ሥራውን በይፋ ያስጀመረው የአቃቂ ቃልቲ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ገልጿል።

የአቃቂ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት የመኸር ሰብል ምርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ የአቃቂ  ቃሊቲ ክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች፣ የማዕከል፣ የክፍለ ከተማና የወረዳው ባለሙያዎች በማስጀመርያ መርሃግብሩ ተሳትፈዋል።

በምግብ ራስን የመቻልና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት አንድም መሬት ፆም ማደር የለበትም በሚል መርህ በከፍተኛ ንቅናቄ የመኸር እርሻ ሥራ እየተሰራ መሆኑን የክፍለ ከተማው የዘርፉ ኃላፊ አቶ አህመድ ዑርጎ ገልፀውልናል።

አክለውም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አርሶ አደሩን በበጀት በመደገፍ፣ ግብዓትና ቴክኖሎጂ በማቅረብ ምርትና ምርታማነትን ለመጨመር ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት አመራሮችና ባለሙያዎችም ዘርፉን በማገዝ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነትና የዜግነት ግዴታ ለመወጣት ዝግጅ መሆናቸውን የገለፁ መሆኑን አቶ አህመድ ዑርጎ ገልፀዋል።

አቶ አህመድ ኡርጎ ለ2018 በጀት ዓመት የመኸር እርሻ  ከ190 ሄክታር በላይ የቦታ ልየታ፣  በትራክተርና በቴክኖሎጂ በመጠቀም የማረስ፣ የምርጥ ዘር እና የአፈር ማዳበሪያ አቅርቦት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። 

አያይዘውም በ2016/17 ምርት ዘመን በመስመር፣ በክላስተርና በኩታ ገጠም በመዝራት ከ17 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ማምረት መቻሉን እና በ2017/18 ምርት ዘመንም የተሻለ ቴክኖሎች በመጠቀምና አስፈላጊውን ማኔጅመንት በመከተል ከ31 ሺህ ኩንታል በላይ ለማምረት  የታቀደ መሆኑን  ተናግረዋል ።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments