የቅዳሜና እሑድ ገበያዎችን ማስቀጠል ተችሏል፡፡

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

የቅዳሜና እሑድ ገበያዎችን ማስቀጠል ተችሏል፡፡

የቅዳሜና እሑድ ገበያዎችን ማስቀጠል ተችሏል፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20 ቀን 2017 ዓ.ም


የግብርና ምርትና አገልግሎቶችን በቅዳሜና እሑድ ገበያ ሸማቹን ከአምራቹ ጋር በቀጥታ በማገናኘት በገበያ ማስተሳሰሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ወ/ሮ ሰርካለም ተፈሪ በሰንበት ገበያ የከተማ ግብርና ምርት አቅርቦት ዛሬም ተጠናክሮ የቀጠለ መሆኑን ገልፀውልናል፡፡


ኃላፊዋ አያይዘውም የእንቁላል ዋጋ በእንስሳት ልማትና ልህቀት ማዕከል በኩል የሚቀርበው በ10 (አሥር) ብር ብቻ እንዲሁም በአምራቾች የሚቀርበው ደግሞ በ14 (አሥራ አራት) ብር እየተሸጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


በተያያዘ ዜና የቄርቆስ ክፍለ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ጽ/ቤት በማህበራዊ ትስስር ገፃችን ላይ የቅዳሜና እሑድ ገበያ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፆልናል፡፡
እንደ ክፍለ ከተማው መረጃ ከጉለሌ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ እንቁላል በአምራቾች በኩል የቀረበው በ14 (አሥራ አራት) ብር እየተሸጠ መሆኑን አሳውቆናል፡፡
የኮሙዩኒኬሽን ሥራ ክፍላችን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ሾላ ገበያ አካባቢ እና ወረዳ 03 ቤላ አካባቢ በነበረው ቅኝ የከተማ ግብርና ምርቶች በቅዳሜና እሑድ ገበያዎች ላይ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጡ መሆኑን ተመልክቷል፡፡


አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ውጤቶች በተለይም እንቁላል ከአምራቹ ለሸማቹ በቀጥታ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑን ቅኝታችን ያሳያል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments