ዕቅድ የሥራ መመሪያ ነው።

image description
- In የእንስሳት ልማት ልህቀት ማዕከል    0

ዕቅድ የሥራ መመሪያ ነው።

ዕቅድ የሥራ መመሪያ ነው።


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም


ዕቅድ የሥራ መመሪያ ተደርጎ ተግባራት ሲፈፀሙ ሪፖርት መነሻው ባለሙያ ይሆናል።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን ከማዕከል እና ከተጠሪ ተቋማት አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች ጋር እየገመገመ ይገኛል።

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ዕቅድ የሥራ መመሪያ ተደርጎ ሲሰራ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ መነሻው ባለሙያ ስለሚሆን ከውሸት የፀዳ ይሆናል ብለዋል።

አያይዘውም ዋና ኮሚሽነሩ በመክፈቻቸው አገልግሎት አሰጣጣችን በስታንዳርድ እየተለካ ከሄደ ሰው ተኮር ሥራችን የነካ እንደሚሆን ገልፀዋል።

ኮሚሽኑ አፈፃፀሙን በየደረጃው እየገመገመ መምጣቱ በበጀት ዓመቱ አቅዶት የነበረውን ዕቅድ ለማሳካት ትልቅ አቅም የፈጠረ መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች የሚቀርበው የመወያያ ሰነድ የእያንዳንዳቸው የዓመት የሥራ ውጤት በመሆኑ በንቃት እንዲሳተፉ በመክፈቻ ንግግራቸው አሳስበው ውይይቱ ተጀምሯል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments