
የከተማ ግብርና ቤተሰብ የከተማ ግብርና ሥራን ባህል ማድረግ አለበት፡፡
የከተማ ግብርና ቤተሰብ የከተማ ግብርና ሥራን ባህል ማድረግ አለበት፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከአጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች ጋር በመሆን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን የማጠቃለያ ግምገማ አድርጓል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ ከተማ ግብርና በአምራች እጆች ከተማችን አዲስ አበባ ላይ ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።
አያይዘውም የልማት ተነሽ አርሶ አደሮችን መልሶ የማቋቋምና የማልማት፣ አርሶ አደሮችን ከከተማዋ ልማት ጋር አብረው እንዲለሙ የማድረግ፣ የከተማ ግብርናን የማስፋፋትና የማጠናከር፣ ደህንነቱ፣ ጥራቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የግብርና ምርትና አገልግሎት ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ የማድረግ ሰፊ ሥራ በበጀት ዓመቱ የተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የኮሚሽኑ ሰራተኞች መታየት አለባቸው ያሏቸውን ከአሰራር፣ ከአደረጃጀት፣ ከጥቅማ ጥቅም፣ ከሥራ ምቹ ሁኔታ አንፃር፣ ከምርትና ምርታማነት ጋር፣ ከመረጃ ጥራትና አያያዝ፣ ከበጀት አጠቃቀምና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነሩ አሰራርን ተከትሎ መስራት፣ ከቅንጅታዊ ተቋማት ጋር ተቀራርቦና ተግባብቶ መስራት፣ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን አምርሮ መታገል ይገባል ብለዋል።
በተጨማሪም ሁሉም የኮሚሽኑ አመራርና ሰራተኛ ከማዕከል እስከ ወረዳ በመናበብ ዕቅድን የሥራው መመሪያ አድርጎ መስራት ያለበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments