አረንጓዴ አሻራ የምናወራለት ሳይሆን በጋራ የምን...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

አረንጓዴ አሻራ የምናወራለት ሳይሆን በጋራ የምንተገብረው የልማት ስራችን ነው፤ አቶ ባዮ ሽጉጤ፡፡

አረንጓዴ አሻራ የምናወራለት ሳይሆን በጋራ የምንተገብረው የልማት ስራችን ነው፤ አቶ ባዮ ሽጉጤ፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22 ቀን 2017 ዓ.ም


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን መዋቅሩን በማስተባበር አጠቃላይ አመራሮችና ሰራተኞች የችግኝ ተካላ መርሃ ግብር አካሂደዋል፡፡ 

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ዓላማ ሀገራችን ኢትዮጵያ ለዜጎቿ ህይወት የተመቸች፤ ጽዱና አረንጓዴ የመኖሪያ ሥፍራን የተጎናጸፈች፣ የአየር ንብረቷ ለሰው ልጅ ተስማሚና ለኑሮ ተስማሚ የሆነች ሀገር እንድትሆን ነው ብለዋል፡፡

በመርሃ-ግብሩም ከ1,250 በላይ የሚሆኑ ችግኞች በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ቀጠና አንድ በተለምዶ ፍቅር ጫካ በተባለው አካባቢ ተከላ ተደርጓል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ለተከታታይ 6 ዓመታት በስኬታማነት በመካሄድ ላይ መሆኑንም ዋና ኮሚሽነሩ ገልፀዋል። 

የአረንጓዴ አሻራ ማኖር ታላቁ ዓላማችንን ስንደርስበት ለመኖር ሳይሆን እየኖርነው የምንደርስበት መሆናችንን በተግባር ለዓለም አረጋግጠናል። ምክንያቱ ደግሞ አረንጓዴ አሻራ የምናወራው ሳይሆን የምንኖረው በመሆኑ ነው፡፡

የኮሚሽኑ አመራሮችና ሰራተኞችም በየዓመቱ ችግኝ ምትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብና በተግባር ለጥቅም ማድረስ እንደሚገባ ዓመት ጠብቆ የሚመጣ ተግባር በመሆኑም እጅግ በጣም የሚጓጉለት እንደሆነና በተከላው እጅግ በጣም መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments