የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራር በእንቁላል ጣይ ዶሮ እ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራር በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን አወያዩ።

የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራር በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን አወያዩ።


አዲስ አበባ (ሐምሌ 22/2017 ዓ.ም)


የኮሚሽኑ ከፍተኛ አመራር በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ዘርፍ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን አወያዩ። 
ውይይቱ የተጀመረው ባለፈው በጀት ዓመት በዘርፉ የነበሩ ጠንካራ ጎኖችንና ድክመት ያለባቸውን ጉዳዮች በሪፖርት በማቅረብ ሲሆን ሪፖርቱን ያቀረቡት በምክትል ኮሚሽነር ማዕረግ የእንስሳት ልማት እና ልህቀት ማዕከል ኃላፊ የሆኑት አቶ አሌክስ ደመቀ በዘርፉ የነበሩትን መልካም ተግባራትና ተግዳሮቶች በዝርዝር አቅርበዋል።
በማህበራት በኩል እንደክፍተት የታዩት የክትትል አናሳነት፣ የቁጠባ ባህል አለመዳበርና ስራውን በኃላፊነት አለመምራት እንዲሁም አሠራርን ጠብቆ አለመስራት ለቀጣይ ትኩረት ተደርጎባቸው መሠራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸው ተነስቷል።
የዘርፉ የልማት ተነሺ አርሶ አደሮች ከከፍተኛ አመራሩ ጋር ስራቸውን መገምገማቸውና ውይይት ማድረጋቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው ትኩረት የሚሹ ያሏቸውን ያጋጠሙ ችግሮችን አንስተዋል። ከተነሱ ችግሮች ውስጥ በዋናነት የመኖ ዋጋ መናር ለስራቸው እንቅፋት መሆኑና አልፎ አልፎ የውሃና መብራት መቆራረጥም እንደሚከሰት ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ በዘርፉ የመጣው ለውጥ በተለይም በማዕከሉ የሚመረተው የእንቁላል ምርት የገበያ ዋጋን ከማረጋጋት ባለፈ ዋጋን እስከመተመን የደረሰ በመሆኑ ማህበራት በስራቸው ሊኮሩ እንደሚገባ ተናግረዋል። የሚያጋጥሙ ችግሮችም በየደረጃው እንዲፈቱ ኮሚሽኑ እንደሚሰራ ጠቁመዋል።
ምንጭ:- የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments