ግብርና በቦታ የማይገደብ በመሆኑ ከተለምዶው እሳ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ግብርና በቦታ የማይገደብ በመሆኑ ከተለምዶው እሳቤ መውጣት ግድ ይላል፡፡

ግብርና በቦታ የማይገደብ በመሆኑ ከተለምዶው እሳቤ መውጣት ግድ ይላል፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም


ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ግብርናን ከተለምዶው በተለየ መንገድ ተግባራዊ ማድረግ የሁሉም የግብርና ቤተሰብ ዕይታና ተግባር መሆን አለበት፡፡


ግብርና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከታገዘ የግብርና ምርቶችን በሚፈለገው መጠንና ጥራት በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ከመቻሉም በላይ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የውጭ ገበያን ታሳቢ ያደረገ አመርቂ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብ ይቻላል።


የከተማ ግብርና አነስተኛ በሆነ ቦታ ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእንስሳት እና የእፀዋት ልማት በማካሄድ ማምረት፣ የተመረቱ ምርቶችን ማቀነባበር፣ የሥራ ዕድል መፍጠር እና ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ማግኘት ነው።


በሽቅብ እርሻ፣ አኳ ፎኒክ፣ ኤሮ ፎኒክ፣ ሃይድሮ ፎኒክ፣ ጣራ ላይ፣ ግድግዳ ላይ፣ በረንዳ ላይ እንዲም አትክልትን በማንኛውም አፈር መያዝ በሚችል አሮጌ እቃ (በጆንያ፣ በርሜል፣ ጎማ፣ ማሰሮ፣ ገንዳ፣ ፌስታል፣ ጠርሙስና በመሳሰሉት) ማልማት ይቻላል፡፡ ተችሏልም፡፡


ዶሮን በዘመናዊ ኬጂ፣ የወተት ላሞችን እና ማድለብን በዘመናዊ ሸድ፣ ንብን በዘመናዊ ቀፎ በቤት ጣራና ግድግዳ ላይ በቀላሉ በቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡
የግብርና ዘርፈ ብዙ የሆነ ሚና ያለው እና በቦታ የማይገደብ በመሆኑ ከተለምዶው እሳቤና ትግበራ በመውጣት ገጠር ላይ ይተገበር የነበረውን ከተማም ውስጥ በስፋት እና በጥልቀት ተግባራው ማድረግ ግድ ይላል፡፡


ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አብዮት ቅርስ ትምህርት ቤት ላይ ተዘዋውረን የተመለከትነው የከተማ ግብርና ሥራ ለሌሎች ጥሩ ልምድ የሚወሰድበት ሆኖ ስላገኘነው ፎቶዎቹን ከዚህ ዜና ጋር ልንጠቀመው ወደናል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡-
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT 
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments