አገልግሎት ሥራ ነው፡፡

image description
- In አርሶ አደር ልማትና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ    0

አገልግሎት ሥራ ነው፡፡

አገልግሎት ሥራ ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 25 ቀን 2017 ዓ.ም


የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ አገልግሎት የተገልጋይን አጠቃላይ ሁኔታ በመረዳት ሰጥቶ የመቀበል መስተጋብ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡

ም/ኮሚሽነሯ ተገልጋይን ዝቅ ብሎ በትህትና ማገልገል ከሁሉ በላይ መባረክ ነው ብለዋል፡፡ ሮብና አርብ ወደ ኮሚሽኑ የሚመጡ ተገልጋዮች አንዳንዶቹ ካለባቸው ተደራራቢ ችግሮች የተነሳ የሚያነሱት ሃሳብ ልብ የሚነካ እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

ከታች እስከ ላይ ያለው የመንግስት መዋቅር፣ ሌሎች አደረጃጀቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ አካላት በጋራ ተባብረው በሚሰሩት ሥራ አገልግሎት የተሳለጠ እንዲሆን ወይም ቅሬታ እንዲያስነሳ ያደርጋል፡፡

አገልግሎት በተቀመጠለት ስታንዳርድ መሰረት ለተገልጋዮ መሰጠት እንዲቻል በአገልጋዮና በተገልጋዮ በኩል የሚጠበቁ መለኪያዎች በቅልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡

ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ እንደ ኮሚሽን አርሶ አደሮች በተለይ በታችኛው መዋቅር ቅሬታዎቻቸው ሳይፈቱላቸው ሲቀሩ አቤቱታዎቻቸውን ይዘው ስለሚመጡ ሮብ እና አርብ እንደ ኮሚሽን ተገልጋይ የሚበዛ መሆኑን አንስተዋል፡፡

እኛም በምልከታዎቻችን የአገልግሎት መስጫ ቀናት ተብለው በተቀመጡ ዕለታት በርካታ ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ የሚመጡ እና በተሰጣቸው አገልግሎት አብዛኞቹ እረክተው የሚመለሱ መሆኑን ተመልክተናል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments