
ሥራን ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ መቀበል የአመራር የመሪነት ሚና ነው፡፡
ሥራን ቆጥሮ ሰጥቶ ቆጥሮ መቀበል የአመራር የመሪነት ሚና ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዘርፍ ከማዕከል እስከ ወረዳ መውረድ ያለበትን የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ተናባቢ በሆነ መንገድ ከዳይሬክተርና ቡድን መሪዎች ጋር በመሆን ካስኪድ አድርጓል፡፡
የዘርፉ ተጠሪ ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ዕቅድን ቆጥሮ በመስጠት ቆጥሮ መቀበል የአመራሩ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም የዘርፉን ዕቅድ ከማዕከል እስከ ወረዳ መውረድ ያለበትን ተናባቢ በሆነ መንገድ ካስኪድ ያደረጉ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በሌላ በኩል እንደ ተቋም በ2018 በጀት ዓመት ትኩረት ተደርጎ የሚሰራባቸውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የመለየትና ስትራቴጃዊ በሆነ መንገድ የማቀድ ሥራ መሰራቱንም ተናግረዋል፡፡
የዘርፉ ዳይሬክተርና ቡድን መሪዎችም በበጀት ዓመቱ የዝግጅት ምዕራፍ ላይ ቀድመው መደበኛና የአመራር ዕቅዶቻቸውን ተናባቢ በሆነ መንገድ ማቀዳቸው የተግባር ምዕራፍ ሥራቸውን ስኬታማ በሆነ መልኩ ለመፈፀም እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ ዕቅዶች ከባለሙያዎችና ከሚመለከታቸው ቅንጅታዊ ተቋማት፣ ባለድርሻ አካላት እና ተገልጋዮች ጋር በቅርቡ የጋራ እንደሚደረጉም በአጽህኖት ገልፀዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments