
ቴክኖሎጂዎች “ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” እየወጡ ነው፡፡
ቴክኖሎጂዎች “ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” እየወጡ ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26 ቀን 2017 ዓ.ም
ዛሬ ዛሬ የምንመለከታቸው የግብርና ቴክኖሎጂዎች ሞፈር፣ ቀንበርና በሬ በመጠቀም የእርሻ ሥራ ሲካሄድ እያየ ላደገና በግብርና ሥራ ውስጥ ለሚገኝ ትውልድ በግብርናው ዘርፍ አዲስ ታሪክ መፃፍ መጀመሩን እንዲገነዘብ ያደርጋሉ፡፡
ድካምን የሚቀንሱ፣ ጊዜንም የሚቆጥቡ የግብርና ቴክኖሎጂዎች በኢትዮጵያ ሥራ ላይ ሳይውሉ ዘመናት በመቆጠራቸው ገበሬው የግብርና ሥራውን ሲያከናውን የኖረው በብዙ ድካም ውስጥ በማለፍ ነው።
ዛሬ አርሶ አደሩን ከኋላቀር የግብርና ሥራ ማውጣት የሚያስችሉ ተስፋ ሰጭ የግብርና ሜካናይዜሽን ሥራዎች ተጀምረዋል፡፡ የግብርና ሜካናይዜሽን የተተገበረባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎችም በአርዓያነት እየተጠቀሱ ነው፡፡
የግብርናውን ዘርፍ ከፍ ወዳለ ደረጃ ለማሸጋገር ከተለመደው አሠራር መውጣት፣ የምርት ስብጥሩን ማስፋትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት መጠቀም፣ ገጠር ላይ ብቻ ይታወቅ የነበረውን ግብርና በከተማም ማስፋት የግድ ይላል፡፡
የከተማ ግብርና አነስተኛ በሆነ ቦታ ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በእንስሳት ልማት ዘርፍ (በዶሮ እርባታ፣ በወተት ከብት እርባታ፣ የንብ ማነብ፣ በዓሣ እርባታ፣ ዳልጋ ከብት ማድለብ፣…) ማርባት እንዲሁም በእፀዋት ልማት ዘርፍ (አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ቅመማ ቅመም፣…) ልማት በማካሄድ ማምረት፣ የተመረቱ ምርቶችን ማቀነባበር፣ ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር እና ምርቱን ለቤት ፍጆታ ከማዋል ባሻገር ለገበያ በማዋል ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ማግኘት ነው።
በሁሉም የከተማ ነዋሪዎች ዘንድ የከተማ ግብርና ሥራ በእጅጉ እየተለመደና ባህል እየሆነ መምጣት አለበት፡፡ ልምድና ተሞክሮዎችም እየተቀመሩ መስፋት መቻል አለባቸው፡፡ ቴክኖሎጂዎችም “ከቤተ-ሙከራ ወደ አዝመራ” መውጣት አለባቸው፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments