
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አቅማችንን አሟጠን እንሰራለን፡፡ አቶ አህመድ ኡርጎ
ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አቅማችንን አሟጠን እንሰራለን፡፡ አቶ አህመድ ኡርጎ
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 28 ቀን 2017 ዓ.ም
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የንግድ እና ኢንዱስትሪ የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ በማሳ ተገኝቶ የመኸር ሰብል እርሻ አዝመራን አዝምሯል፡፡
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በተለያዩ ወረዳዎች የ2017/2018 በጀት ዓመት 3ኛ ዙር የ90 ቀናት የሌማት ትሩፋት፣ ከተማ ግብርና እና የመኸር ሰብል እርሻ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በዛሬው ዕለት የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ቱሪዝም የምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የወረዳ አንድ አስተባባሪ አመራሮችና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው የመኸር የሰብል ዝመራውን አበረታተዋል።
በያዝነው የ2017/18 ምርት ዘመን የመኸር ሰብል ምርት 1,090 ሄክታር መሬት እንደሚለማ የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አህመድ ኡርጎ ተናግረዋል፡፡
የ2017/2018 በጀት ዓመት የመኸር ሰብል ምርት በከፍተኛ አመራሩ እና ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ጠንካራ ክትትል እና ድጋፍ በማድረግ እየተሰራ መሆኑንም አቶ አህመድ ኡርጎ ያደረሱን መረጃ ያመለክታል፡፡
በዚህ ልክ በተደራጀ መንገድ አርሶ አደሩን የመደገፉ እና መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ በሌሎች ክፍለ ከተሞች ላይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments