በአንድ ወር ውስጥ እስከ 86 ኪ.ግ ድረስ የክብ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

በአንድ ወር ውስጥ እስከ 86 ኪ.ግ ድረስ የክብደት ለውጥ ያስመዘገቡ የዳልጋ ከብቶች አሉ

በአንድ ወር ውስጥ እስከ 86 ኪ.ግ ድረስ የክብደት ለውጥ ያስመዘገቡ የዳልጋ ከብቶች አሉ


አዲስ አበባ (ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም)


የእንስሳትን ክብደት መከታተል በእንስሳት ማድለብ ዘርፍ የየዕለት ክትትልና ድጋፍ አንድ አካል ነው። የእንስሳቱን ክብደት ጭማሪ መከታተል ምርታማ ያልሆኑ እንስሳትን ለይቶ እርምጃ ለመውሰድ አስፈላጊ ነው።


በዚህ ዙር በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል ከወር በፊት ወደ ማዕከሉ የገቡ እንስሳት በወቅቱ የክብደት ልኬት የተወሰደላቸው ሲሆን በድጋሚ ከወር በኋላ ተወስዶላቸዋል። 


በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እስከ 86 ኪ.ግ ድረስ ለውጥ ያሳዩ እንስሳት የመኖራቸውን ያክል በተለያየ ምክንያት የሚፈለገውን ያክል ለውጥ ያላመጡ እንስሳትም አሉ። እነዚህን እንስሳት ለይቶ ለማስወጣት ክብደት መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልፃሉ።


ምንጭ፦ የእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments