
መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡
መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ የሁላችንም ኃላፊነት ነው፡፡
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 03 ቀን 2017 ዓ.ም
የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን አጠቃላይ አመራርና ሰራተኞች የፍራፍሬ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡
ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዩ ሽጉጤ ዛሬ እየተከልን ያለው የፍራፍሬ ችግኝ ከአረንጓዴ ልማትነቱ ባሻገር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራን ያለው የመደበኛ ሥራችን አካል ነው ብለዋል፡፡
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ለምግብነት የሚሆኑ ከ2 ሺህ በላይ የፍራፍሬ ችግኞች ተተክለዋል፡፡
የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ በአርሶ አደር ማሳ ላይ የተተከለ በመሆኑ በቀጣይ ለመንከባከብም አመች መሆኑን ዋና ኮሚሽነሩ ገልፀዋል፡፡
በችግኝ ተከላ ሂደቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩት አመራርና ሰራተኞችም በዛሬው ዕለት የተካሄደው ተከላ በዓይነቱ የተለየ እና በቀጣይ ለመንከባከብም ምቹ በመሆኑ በአግባቡ እንከባከባለን ብለዋል፡፡
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments