ስራን ቆጥሮ በመስጠት ቆጥሮ መቀበል የመሪነት ሚ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ስራን ቆጥሮ በመስጠት ቆጥሮ መቀበል የመሪነት ሚና ነው፡፡

ስራን ቆጥሮ በመስጠት ቆጥሮ መቀበል የመሪነት ሚና ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 06 ቀን 2017 ዓ.ም


የኮሚሽኑ አራቱም ዘርፎች ዕቅዳቸውን እስከታችኛው መዋቅር ካስኪድ አድርገው አውርደዋል፡፡

የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ዘርፎች የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን ካስኪድ በማድረግ በየዘርፋቸው እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በማውረድ የመፈራረም ሥነ-ስርዓት አካሂደዋል፡፡
ዕቅድን በጊዜ፣ በጥራት እና በተገቢው መጠን ከበጀት ጋር አጣጥሞ ማቀድና ለሚመለከታቸው አካላት ቆጥሮ መስጠት የተግባር ምዕራፍን በግማሽ የመሄድ ያክል ነው፡፡

አመራር ዕቅዱን ካስኪድ አድርጎ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ካወረደ በቀጣይ ለሚያደርገው የድጋፍና ክትትል፣ የቁጥጥር፣ የማስተባበር፣ የግምገማ፣ የምዘና እና የተጠያቂነት አሰራር ሥርዓትን በውጤታማነት ለመምራት ያስችለዋል፡፡

የአራቱም ዘርፍ ኃላፊዎች ዳይሬክቶሬቶችና ቡድን መሪዎች በአስቼኳይ ለባለሙያዎቻቸው ዕቅዳቸውን ቆጥረው በመስጠት የተግባር ሥራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments