ግብርና  ማለት  በአፈርና  በውኃ  ላይ  መዘመ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ግብርና  ማለት  በአፈርና  በውኃ  ላይ  መዘመን  ማለት  ነው!!

ግብርና  ማለት  በአፈርና  በውኃ  ላይ  መዘመን  ማለት  ነው!!

 የሀገራችን  ኢትዬጵያ  ግብርና  ወይም  እርሻ  ለበርካታ  ክፍለ  ዘመናት  ለኢትዬጵያ  ህዝቦች  ባለ  ውለታ ፣ ለሀገሪቱ  ፖለቲካዊ  ኢኮኖሚያዊ  ዋልታና  መከታ፤  ለገጽታ  ግንባታ  መታያና  መመልከቻ፤ለውጭ  ወራሪ  ጠላት   ሀይል  አቅምና  መሞገቻ  ፣ የምርት  ውጤት   ሲትረፈረፍ  መደሰቻ ብቻ  ‹‹ግብርና  እና  ኢትዬጵያ    ኢትዬጵያና  ግብርና›› ከስረ  መሰረቱ  ታሪካዊ   ትስስር  ያላቸው   አብረው የነበሩ  አሁንም  አብረው  ያሉ   ወደፊትም   ባህሪያቸውን  እዬቀያየሩ   የሚኖሩ  ሁለት   የማይነጣጠሉ  አንድ  አካሎች  ናቸው ፡፡

የአብዛኛው  የዓለማችን  ሀገራት  ታሪካዊ  ዳራ  ስንመለከት   እንደ  አፍሪካ  ወይንም  ደግሞ እንደ  ኢትዬጵያ  በተፈጥሮ  ሀብትና  ፀጋ  ማለትም   ተስማሚ  አየር  ንብረት፤ ክረምትና  በጋ  ሲያቆራርጥ  የሚፈስ  የውኃ አካላት፤  ታላላቅ  የተፈጥሮ  ደንና  ተራሮች፤  የተፈጥሮ  ማዕድናት፤የእንስሳት  ሀብት ልማት፤  ሰርቶ  የማይታክት  ታታሪና  ጠንካራ  አርሶ  አደር  እና  የመሳሰሉት  የተፈጥሮ  ፀጋ    የተቸረው ሀገር  ወይም  ክፍለ  ዓለም  ያለ  ቢሆንም  የኢትዬጵያ  ግን የበለጠ ደስ  ያሰኛል ፡፡
ከዛሬ ብዙ ዓመታት ወደ ኋላ ተጉዘን በምናስብበት ጊዜ የህዝብ ቁጥራችን ዝቅተኛ ቁጥር በነበረበት ወቅት ሲመረት የነበረው የግብርና ምርታማነት አሁንም ላይ እንደዚያው ቢሆን ኑሮ ህዝባችን መግቦ የማኖር ብቻም ሳይሆን ሀገር እንደ ሀገር ሊቀጥል ይችል ነበርን? ግን ደግሞ ከዚህ በላይ ማደግ ነበረበት ከሆነ አወ ነው መልሱ፡፡


ምንጭ፡-ማህበራዊ  ሚዲያ


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments