እያንዳንዳችን የምንፈፅመው ተግባር ደግ ወይም መ...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

እያንዳንዳችን የምንፈፅመው ተግባር ደግ ወይም መጥፎ መሆኑ የሚታወቀው በውጤቱ ነው፡፡

እያንዳንዳችን የምንፈፅመው ተግባር ደግ ወይም መጥፎ መሆኑ የሚታወቀው በውጤቱ ነው፡፡


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 13 2017 ዓ.ም


ሥነ-ምግባር ማለት የሁለት ቃላት ጥምር ውጤት ነው፡፡ “ሥነ” የሚለው ቃል “ሠነየ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የወጣ ሲሆን፤ ያማረ፣ መልካም የሆነ፣ ደስ የሚያሰኝ፣ በለጠ፣ ተሻለ ማለት ነው፡፡ ምግባር የሚለው ደግሞ “ገብረ” ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም ሥራ፣ ፈጠራ፣ ድርጊት፣ ክንውን ማለት ነው፡፡ 

በአጠቃላይ ሥነ-ምግባር ማለት መልካም፣ የተገነባ፣ የተፈቀደ፣ የተወደደ፣ ያማረ ሥራ ወይም ድርጊትን የሚያጠና የፍልስፍና ዘርፍ ሲሆን አንድን ነገር ትክክል ነው ወይም አይደለም ብለን እንድንጠራ የሚያደርገን እሴት ነው፡፡ በእንደዚህ መልኩ ጠለቅ ብሎ የተነተነው ሥነ-ምግባርም በህይወታችን ዋጋ ልንሰጣቸው ከሚገቡን ነገሮች አንዱ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡

እያንዳንዳችን የምንፈፅመው ተግባር ደግ ወይም መጥፎ መሆኑ የሚታወቀው በውጤቱ ነው፡፡ ውጤቱም ያማረ እና የተዋበ የሚሆነው በመልካም ሥነ-ምግባር ላይ ተመርኩዞ ከተሠራ ብቻ ነው፡፡ ይሄንን ውጤቱ ያማረ ተግባር ለመፈፀም ደግሞ መልካም የሆነ የሙያ ሥነ-ምግባር ያስፈልጋል፡፡ 

ሆኖም ሁሉም ዜጋ ለሚሰራው ስራ የስነ-ምግባር መርሆችንና እሴቶችን በመከተል ሀገራዊ፣ ቤተሰባዊና ግላዊ ግዴታዎቹን በመልካም ሥነ-ምግባር ለሀገር ልማትና ዕድገት አስተዋፆውን ማበርከት ይገባል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments