የተሟላ መረጃ ያላቸው በመመሪያው መሰረት ይስተና...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

የተሟላ መረጃ ያላቸው በመመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ:: ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ

የተሟላ መረጃ ያላቸው በመመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ:: ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14 ቀን 2017 ዓ.ም


በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ነዋሪ የሆኑ በተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች ምክንያት ከይዞታቸው  የተነሱ አርሶ አደሮች  በምዝገባና ልየታ  መመሪያው መሰረት አልተስተናገድንም ሲሉ ቅሬታቸውን ለኮሚሽኑ አቅርበወል፡፡

አገልግሎት ፈልገው ወደ ኮሚሽኑ የመጡት ተገልጋዮች በልማት ምክንያት ከይዞታቸው መነሳታቸውን እና አሁን ላይ በልዩ ሁኔታ እየተካሄደ ባለው ምዝገባና ልየታ ሂደት በመመሪያው ላይ የተቀመጡ መስፈርቶችን አታሟሉም ተብለን ልንስተናገድ አልቻልንም ሲሉ ሃሳባቸውን አቅርበዋል፡፡

የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ የምዘገባና ልየታ መመሪያ ከመጽደቁ በፊት በእናንተው በአርሶ አደሮች እና በተወካዮቻችሁ አማካኝነት ውይይት ተደርጎበታል፤ ከ1986 ዓ.ም እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ የተነሱ አርሶ አደሮችና ያነሳቸው ፕሮጀክ ተጠቅሶ የተጻፈ ደብዳቤ ያለው፣ የካሳ ክፍያ ማስረጃ እንዲሁም ካሳ ባይከፈላቸውም ከይዞታቸው ስለመሆናቸው በህጋዊ ተቋም የተረጋገጠ ማስረጃ ያለቸው አርሶ አደሮች በመመሪያው መሰረት ይስተናገዳሉ ብለዋል፡፡

አያይዘውም ሁሉም ከህግ በታች በመሆኑ መመሪያው ከሚፈቅደው ውጭ የሚሰራ አንዳችም ነገር አይኖርም፤ በዚህ አግባብ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ሁላችሁም ከኮሚሽኑ ጎን አብራችሁ ልትቆሙ ይገባል ብለዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments