
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር የጋራ ተደርጓል።
የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር የጋራ ተደርጓል።
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 15 ቀን 2017 ዓ.ም
በእንስሳት ልማት እና ልኅቀት ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ተግባራትን ከአጠቃላይ ሠራተኞች ጋር የጋራ ማድረግ ተችሏል።
ማዕከሉ እንደተጠሪ ተቋም የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀምን መነሻ በማድረግ ለ2018 በጀት ዓመት እንዲያከናውን በኮሚሽኑ የወረደለትን ዕቅድ በዝርዝር ለአጠቃላይ ሠራተኞች ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ የማዕከሉ ሠራተኞች ሃሳብ ያነሱ ሲሆን ከተነሱ ሃሳቦች መካከል ዕቅዱን ለማሳካት የግብዓት አቅርቦት፣ የማህበራት የስራ ተነሳሽነት እና መሠል ችግሮች ተቀርፈው በባለሙያ እና በአመራር ቁርጠኛ የሆነ ድጋፍና ክትትል ዕቅዶችን መፈፀም እንደሚገባ ተነስቷል።
የማዕከሉ ኃላፊ አቶ አሌክስ ደመቀ የተያዙ ዕቅዶችን በላቀ አፈፃፀም ለመስራት የራስ ተነሳሽነት ወሳኝ እንደሆነና ሁሉም ሠራተኛ ካለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀማችን በመነሳት አቅምን አሟጦ በመጠቀም መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ባለፈው በጀት ዓመት ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታትና መፍትሔዎችን በማስቀመጥ ያለንን የሰው ኃይል በመጠቀምና በቅንጅት በመስራት የማዕከሉን ግብ ለማሳካት ሁሉም መረባረብ እንደሚገባ ገልፀዋል።
መረጃው፦ የእንስሳ ልማትና ልህቀት ማዕከል ነው።
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments