ጤንነቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምር...

image description
- In የከተማ ግብርና ልማት ዘርፍ    0

ጤንነቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡

ጤንነቱ፣ ደህንነቱና ኃይጅኑ የተጠበቀ የሥጋ ምርት ለማህበረሰቡ እንዲቀርብ ይደረጋል፡፡


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም


በአዲስአበባ ቄራ ሥጋ ምርመራና ሰርተፊኬሽን ቡድን የፍልሰታ ፆም ፊችን አስመልክቶ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡


ከነሐሴ 14-16 ቀን 2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ከጥራት ቁጥጥር ባለሙያ ጋር በመሆን የእርድ እንስሳት በረቶች፤ እርድ ክፍሎች፤ እርድ ክዋኔ መሳሪያዎች፤ ምድረ ጊቢና የሥጋ መጓጓዣ መኪናዎችን የፀረ-ተዋስያን ሪጭት ( Disinfection) ስራ መሰራቱን የሥጋ ምርመራ ቡድኑ ገልጿል፡፡


በተያያዘም ዘርፉ የዛጉ፣ የበሰበሱ ጋንቾችና ሥጋ ማንጠልጠያ ብረቶች እንድቀየሩ መደረጉን በላከልን መረጃ ገልጿል፡፡ ሌላው ካራከስ የሚያነሱ ሞቶሮች እንዲገጠሙ ተደርጓል ብለዋል፡፡


ከእርድ እንስሳት ቅበላ ሰዓትን ጋር በተያያዘ አርብ በ16/12/2017 ዓ.ም ከ ጧቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት የሚከናወን ሲሆን እርድ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት የሚጀምር ይሆናል፡፡


ሳኒቴሽንና ኃይጂንን በተመለከተ እርድ ክፍሎቹ እርዱ ሳይቋረጥ ቶሎቶሎ በውሃ ብቻ እንዲፀዱ ከቄራ ድርጅቱ እርድ ክፍል አገልግሎት ይረክቶሬት ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡


በዓሉን ምክንያት አድርጎ ከአርብ ጀምሮ ከፍተኛ ጫና ስለሚኖር ባለሙያዎች በመተጋገዝ እንዲሰሩ የጋራ ተደርጎ ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያሳያል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments