ይህንን ያውቁ ኖሯል???
ይህንን ያውቁ ኖሯል???
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም
የእጽዋት ኳራንታይን ስንል እጽዋትና የእጽዋት ውጤቶች ለተጨማሪ ኢንስፔክሽን ወይም ለማከም ኦፊሴላዊ በሆነ መንገድ ለተወሰነ ጊዜ ማግለል ወይም ዘርንና እጽዋትን ከሚጎዱ ሕይወት ያላቸው ተባዮች ከአንድ አገር ወደ ሌላ አገር እንዳይገባ ለመከላከል የሚደረግ የቁጥጥር ተግባር ነው፡፡ ቁጥጥሩ ወደ አገር ውስጥ በሚገቡ፣ ወደ ውጭ አገር በሚላኩ እና በአገር ውስጥ በሚዘዋወሩ እጽዋት፣ የእጽዋት ውጤቶችና ሌሎች ቁጥጥር በሚደረግባቸው ቁሳቁሶች ላይ ይካሄዳል፡፡
ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ገቢ ምርቶችን ስንመለከት በአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ በዋናነት ወደ አገር ውስጥ የሚገቡት የአፈር ማዳበሪያ እና የእርሻ ኬሚካሎችን ሲሆኑ እነዚህን በብዛት የምናመጣባቸው አገሮችም ቻይና፣ ሆላንድ፣ ሕንድ፣ ኖርዌይና ጀርመን ናቸው፡፡ እነዚህ ሲገቡ የሚያመጡት ሰነድ ላይ አስፈላጊ ነገሮች መሟላታቸውን ካረጋገጥን በኋላ ጉሙሩክ ጣቢያ በመገኜት በሰነዱ መሰረት መሆናቸውን አካላዊ ምልከታ በማድረግ ሕጉን ጠብቆ የገባ መሆኑን ስናረጋግጥ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ መልቀቂያ እንሰጣለን፡፡ ሌላኛው የኳራንታይን ጣቢያው የሚሠራው ሥራ አስመጭና ላኪዎች ንግድ ፍቃድ አውጥተው በዘርፉ ላይ ከመሰማራታቸው በፊት በባለሥልጣን መ/ቤቱ የተቀመጡ መሥፈርቶች መሟላታቸውን በማረጋገጥ ለባለሥልጣን መ/ቤቱ የብቃት ማረጋገጫ እንዲሰጣቸው እንጽፋለን፡፡ ባለሥልጣን መ/ቤቱም ለንግድ ሚ/ር ንግድ ፍቃድ እንዲሰጣቸውና ንግድ ፍቃድ አውጥተው በዘርፉ እንዲሰማሩ ደብዳቤ ይጽፋል ማለት ነው፡፡
በኳራንታይን ጣቢያው 4ኛው ሥራችን የሕክምና አገልግሎት ሲሆን በዚህ ዘርፍ ወደ ውጭ አገር የሚላኩ እህሎች በአግባቡ ታክመው 72 ስዓት ታሽገው ከተባይ ነጻ ሆነው እንዲሄድ የምናደርግበት የአሰራር ሥርዓት ነው፡፡ በአጠቃላይ የአዳማ የእጽዋት ኳራንታይን ጣቢያ እነዚህ ከላይ የተገለጸውንና ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
ምንጭ፡- ግብርና ሚኒስቴር
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments