ደህንነቱ  የተጠበቀ  የስጋ  ምርት  ለህበረተሰ...

image description
- In ሰርተፍኬሽን፣ ኢንስፔክሽን፣ኳራንቲንና ሬጉላቶሪ ዘርፍ    0

ደህንነቱ  የተጠበቀ  የስጋ  ምርት  ለህበረተሰቡ   እንዲቀርብ በትኩረት እንሰራለን፡፡

ደህንነቱ  የተጠበቀ  የስጋ  ምርት  ለህበረተሰቡ   እንዲቀርብ በትኩረት እንሰራለን፡፡


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 20 ቀን 2017 ዓ.ም


የሰርተፍኬሽን  ኢንስፔክሽን  ኳራንቲንና  ሬጉላቶሪ  ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት  ከባለድርሻ  አካላት  ጋር  በቅንጅት  የሚከናወኑ  ተግባራት   እቅድ ላይ   ተፈራረሙ፡፡

የዘርፉ  ኃላፊ  ፀጋ ለማ (ዶ/ር)  ተከታታይ የመረጃ ልውውጥ ስርዓት እንዲኖር በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካካል የመረጃ ልውውጥ ስርዓት መዘርጋት አለበት ብለዋል፡፡

አያይዘውም  የባለድርሻ አካላት ሚና  የህብረተሰቡ  ተጠቃሚነት ላይ በጋራ ለመስራት እና አፈፃፀሙንም በተገቢው በመገምገም አዎንታዊ የሆነ እርምጃዎችን በየጊዜው እንዲወስዱ ለማድረግ  እንደሆነ ገለጹ፡፡

የሸገር ከተማ መዘጋጃቤት፣የአዲስ አበባ ከተማ ቄራዎች ድርጅት፣የካራአሎ ኃላፊነቱ የተወሰነ  የግል ማህበር ቄራዎች ድርጅት፣የአዲስ አበባ  ልኳንዳቤቶች ማህበር እና አሪፈታ ኃላፊነቱ የተወሰነ  የግል ማህበር ስጋ ማጓጓዣ የትስስር ሰነድ  የመፈራረም ሥነ-ስርዓት አካሂደዋል፡፡

በስጋ መሸጫ  ተቋማትና  በቄራ  ድርጅቶች አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮች ላይ በመስራት ደህንነቱ የተጠበቀ የስጋ ምርት ለህበረተሰቡ  እንዲቀርብ  ለማስቻል  በቅንጅት ለመስራት በመጋበዛቸው ደስተኞች እንደሆኑ   በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ወቅት  ባለድርሻዎቹ ገልጸዋል፡፡


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments