እውቅናና ሽልማት ለልማት እና ለበለጠ ውጤት  ት...

image description
- In አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን    0

እውቅናና ሽልማት ለልማት እና ለበለጠ ውጤት  ትልቅ አቅም ነው።

እውቅናና ሽልማት ለልማት እና ለበለጠ ውጤት  ትልቅ አቅም ነው።


አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 22 ቀን 2017 ዓ.ም


የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ከማዕከል እስከ ወረዳ ላለው መዋቅር እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል።

ኮሚሽኑ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምን መነሻ አድርጎ ከ11ዱም ወረዳዎች 1ኛ ለወጡ 11 ወረዳዎች፣ ከማስፋፊያ እና ከማህል ክፍለ ከተሞች መካከል 1ኛ ለወጡ ሁለት ክፍለ ከተሞች በድምሩ ለ13 ተቋማት የሞተር ሳይክል ሽልማት አበርክቷል።

ሁለተኛ ለወጡ 11 ወረዳዎች እና ሁለት ክፍለ ከተሞች በድምሩ 13 ላፕቶፖች እና የሦስተኛ ደረጃ ለያዙ ከወረዳና ከክፍለ ከተሞች ደግሞ ፕሪንተር እና ዋንጫዎችን በሽልማት አበርክቷል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ለማዕከላት፣ ለዳይሬክቶሬቶች፣ ለቡድኖች እና ለፈፃሚዎች ቀደም ካለው ጊዜ በተለየ መልኩ አበረታች የሆኑ ሽልማቶችን ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የተሰጡ ሽልማቶች ለመጭው የ2018 በጀት ዓመት ሥራችን አቅም ናቸው ብለዋል።

አያይዘውም በዕለቱ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድን በጋራ ማየታችን እና የ2017 በጀት ዓመት እውቅናና ሽልማት ማካሄዳችን ጥንካሬዎቻችንን አጠናክረን ለማስቀጠል እና ክፍተቶቻችንን የዕቅዳችን አካል አድርጎ ለመሄድ ያግዛል ብለዋል።

እውቅናና ሽልማት የተሰጡ ተቋማትም የዘንድሮው ከመቸውም የተለየና ደስታን የፈጠረልን ነው ብለዋል። እውቅናና ሽልማትም በዚህ ልክ መሰጠቱ ለስራችን ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራል ብለዋል።

ዋና ኮሚሽነር አቶ ባዮ ሽጉጤ የተሰጠው ሽልማት ለተቋማትና ለግለሰቦች ሲሆን ሁሉም በነበራቸው የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና መሰረት መሆኑን አንስተው ይህ በቀጣይ ለሁሉም አመራርና ሰራተኞች ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ተናግረዋል።


Comments

Nothing was found.

Leave Your Comments