
ግብርና ከማምረትም በላይ ነው!፡፡
ዜና ትንታኔ
ግብርና ከማምረትም በላይ ነው!፡፡
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም
ሀገራችን ለግብርና ልማት የተሰጠች ሀገር ናት። ለዘርፉ ውጤታማነት ተስማሚ የአየር ንብረት፣ በቂ የገጸ ምድርና የከርሰምድር ውሃ፣ ለም መሬትና አምራች የሰው ሃል ያላት አገር መሆኗ አያከራክርም።
ከተማችን አዲስ አበባ ደግሞ ለከተማ ግብርና ሥራ እጅግ በጣም ምቹና ሊያሰራ የሚችል ገፀ-በረከት ያላት ናት፡፡ ዙሪያዋ በአርሶ አደሮች የታጠረች፣ ኗሪዋ ለግብርና ሥራ አዲስ ያልሆነ፣ ለዘመናዊ ግብዓትና ቴክኖሎጂ እጅግ በጣም ቅርብ የሆነች ናት፡፡
በመሆኑም የሀገራችን ብሎም የከተማችን ዜጎች የህልውና መሠረት የሆነው የግብርና ዘርፍ "ከማምረትም በላይ ነው" ቢባል ማጋነን አይሆንም።
ስለሆነም የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ የሁሉም አካል የሞት የሽረት ጉዳይ መሆኑን ለአፍታም ቢሆን መዘንጋት የለብንም።
የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዳይ በግብርናው ምርታማነት ላይ የተመሰረተ ነው። ሌላው የኢንዱስትሪው እድገትም ቢሆን የሚወሰነው በግብርናው ምርታማነት ልክ ነው።
ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የኑሮው ውድነት ከዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ ጋር ሊመጣጠን የሚችለው የዘርፉን ምርታማነት በተፈለገው ደረጃ ማሳደግ ሲቻል ብቻ መሆኑን መረዳት ይገባል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን የዘርፉን ምርታማነት ማሳደግ የሚያስችሉ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅርቦትና በዘርፉ የተሰማሩ የግብርና ቤተሰብ በእውቀትና በአሰራር ብቁ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
የከተማዋን ነዋሪ የግብርና ቤተሰብ ታሳቢ ያደረጉ ምርትን በእጥፍ የሚጨምሩ፣ የአርሶ አደሩንም ጊዜና ጉልበት የሚቆጥቡ የተለያዩ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አቅርቦት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የግብርናውን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ከመጠቀም በተጨማሪ በሌማት ትሩፋትና በመደበኛው የግብርና ሥራ የግብርናውን ቤተሰብ አቅም የመገንባት፣ ግንዛቤ የማስጨበጥ፣ ልምድና ተሞክሮዎችን የማስፋት ሥራ በስፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡
ግብርና ከማምረትም በላይ ነው!፡፡
ለበለጠ መረጃ
YouTube ➲ https://bit.ly/4hnxoMs
Telegram ➲ https://bit.ly/4h2cPVT
Facebook ➲ https://bit.ly/4gjsu1M
Tiktok ➲ https://bit.ly/4gdXK2o
Comments
Nothing was found.
Leave Your Comments